ባለፉት 3 አመታት ብቻ በአፍሪካ 7 የመፈንቅለ ግልበጣዎች ተካሂደዋል
የፖለቲካ ስልጣንን በሀይል ለመንጠቅ የሚደረጉ ሙከራዎች እና ሴራዎች ቀደም ብሎም የነበሩ የሰው ልጅ የታሪክ አካል ናቸው፡፡
መፈንቅለ መንግስት የፖለቲካ ስርአት እና የመንግስት አስተዳደር ተቀይሮ በሚገኝበት በዚህኛው ዘመንም አልቀረም፡፡
ከ1950 ጀምሮ እስካሁን ባለው ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ 492 የመፈንቅለ መንግስት ሙከራዎች የታካሄዱ ሲሆን፥ 245ቱ ሰኬታማ ነበሩ።
በ74 አመታት ውስጥ 220 የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በማድረግ አፍሪካ ቀዳሚዋ አህጉር ናት፤ ከዚህ ውስጥ 109ኙ የተሳኩ ነበሩ።
ከ54 የአፍሪካ ሀገራት 45ቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎባቸዋል።
ከ2021 በፊት በነበሩት አስርት አመታት በአህጉሪቱ በአማካይ በአመት አንድ መፈንቅለ መንግስት ይከናወን ነበር።
ባለፉት ሶስት አመታት ግን ሰባት የተሳኩ የመንግስት ግልበጣዎች መካሄዳቸው የችግሩ አሳሳቢነት እየጨመረ መሄድን አመላክቷል።
ሱዳን 18 የመፈንቅለ መንግስት በማስተናገድ ቀዳሚዋ ስትሆን 6 ያህሉ ስኬታማ ነበሩ።
ከ1950 እስከ 2024 በርካታ የመፈንቅለ መንግስት የተካሄደባቸው አህጉራትን ይመልከቱ፦