ስራ አጥነት፣ ሙስና፣ ማህበራዊ ቀውሶችና የውጭ ሀገራት ተጽዕኖ ለመፈንቅለ መንግስት ሰፊ አበርክቶ አላቸው ተብሏል
የኒጀር መንግስት በተገለበጠ በአምስተኛ ሳምንቱ የጋቦን መንግስትን በጦሩ መሪዎች ተመሳሳይ እጣ ደርሶታል።
የጋቦን ፕሬዝዳንት አሊ ቦንጎ በመኖሪያቸው እንደታፈኑ ተናግረዋል።
ባለፈው እሁድ የተደረገውን ምርጫ እንዳሸነፉ የተነገረላቸው ፕሬዝዳንት ቦንጎ የድሉ ዜና በብሄራዊ ቴሌቭዥን በተነገረ በደቂቃዎች ልዩነት የሀገሪቱ ወታደሮች ስልጣን መቆጣጠራቸውን አስታውቋል።
ጋቦናዊያን በመንግስት ግልበጣው ደስታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል። ገልባጩ ወታደራዊ መንግስት አሊ ቦንጎ ለምርጫው ደህንነት የዘጉትን የኢንተርኔት አገልግሎት መልሷል።
ተገልባጩ አሊ ቦንጎ ኢንተርኔትን ተጠቅመው ባስተላለፉት መልዕክት ወዳጆቻቸው እንዲጮሁላቸው ጠይቀዋል።
ቢቢሲ በዘገባው ፕሬዝዳንቱና ሌሎችም የአፍሪካ መሪዎች ሳይጠብቁት መፈንቅለ መንግስት ገጥሟቸዋል ብሏል።
የኒጀር ግልበጣ ለምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ "የግልበጣ ወረርሽኝ" መጨረሻ እንዳልሆነ አመላካች ነበር።
ቡርኪናፋሶ፣ ቻድ፣ ጊኒና ማሊ የመሰሉ ሀገራት በምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ ምን እየሆነ ነው? የሚለውንና የፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ተገዥዎች ለምን ግልበጣው ጠናባቸው? የሚለውን መጠየቅ የግድ ብሏል።
ያለፈው ሦስት ዓመት በአምስት ሀገራት ሰባት መንግስት ግልበጣን አስተናግዷል።
የሀገራቱ ሁኔታና አካሄድ ወታደሩ ጣልቃ እንዲገባ ጉትጎታ እና ብዙ ጊዜ የከተማውን ህዝብ በተለይም ወጣቶችን ያበሳጩባቸው የተለመዱ ምክንያቶችን ፈጥሯል።
በአብዛኛዎቹ የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ወጣቶች በህጋዊ መንገድ ቢመረጡም ባህላዊውን የፖለቲካ መደብ ይቃወማሉ።
እንዲህ አይነቱ ብስጭት፣ ስራ አጥነት፣ ከፍተኛ ሙስናና ሌሎችም ማህበራዊ ችግሮች ተደምረው ግልበጣን ብቸኛ አማራጭ እያደረገው ነው።