የደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዙማን ይግባኝ ውድቅ አደረገ
ፍርድ ቤቱ ጃኮብ ዙማ በጤና እክል ምክንያት ምህረት መደረጉ ከህግ ውጪ ነው በማለት ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ አዟል
ዙማ በፈረንጆቹ 2018 በስልጣን ላይ በቆዩባቸው አስር ዓመታት በመንግስት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ለመመስከር አሻፈረኝ በማለታቸው 15 ወራት እስራት ተፈርዶባቸዋል
የደቡብ አፍሪካ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ በጤና እክል ምክንያት በነፃ እንዲለቀቁ መወሰኑ ህገወጥ ነው ብሏል።
ዙማ ፍርድ ቤት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት ለመጨረስ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተወስኖባቸዋል።
ዙማ ባለፈው ዓመት የ15 ወራት እስራት የተፈረደባቸው በፈረንጆቹ 2018 ሲሆን፤ በስልጣን በቆዩባቸው አስር ዓመታት ውስጥ በመንግስት ከፍተኛ የሙስና ወንጀል ምርመራ ለመመስከር የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ችላ በማለታቸው ነው።
ዙማ የቅጣቱን ትንሽ ክፍል ብቻ ከጨረሱ በኋላ በመስከረም 2021 በህክምና ተፈተዋል ተብሏል።
ነገር ግን ከተፈቱ ከወራት በኋላ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የምህረት ውሳኔውን ወደ ጎን በመተው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ወደ እስር ቤት እንዲመለስ ማዘዙን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዙማ ይህን የፍርድ ቤት ውሳኔ ይግባኝ ቢጠይቁም ዙማ በህግ የእስር ጊዜያቸውን አልጨረሱም በሚል በድጋሜ እስር ቤት ይገባሉ ተብሏል።
ይህን ለማድረግ ዙማ ወደ ኢስኮርት ማረሚያ ማዕከል መመለስ አለባቢ ሲል የይግባኝ ሰሚው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርዱን በይኗል።
ፍርድ ቤቱ የብሄራዊ የማረሚያ አገልግሎት ኮሚሽነር የህክምና ይቅርታ ቦርድ የተሰጠውን ምክር በመቃወም ጃኮብ ዙማ ህገ-ወጥ መሆኑን አረጋግጧል።
"በማንኛውም ሊታሰብ በሚችል መልኩ የኮሚሽነሩ ውሳኔ ህገ-ወጥ እና ኢ-ህገ መንግስታዊ" ነው ብሏል ብይኑ።
ሮይተርስ የጃኮብ ዙማ ፋውንዴሽን አስተያየት እንዲሰጥ ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።