መንግስት በትግራይ ያሉ አየርመንገዶችን እና የፌደራል መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል
የህወሓት የተደራዳሪ ቡድን ደቡብ አፍሪካ መድረሱ ተገልጿል፡፡
የህወሓት የተደራዳሪ ቡድን በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው ድርድር ላይ ለመሳተፍ ደቡብ አፍሪካ መድረሳቸውን የህወሓት አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት በትዊተር ገጻቸው ጽፈዋል፡፡
በፌደራል መንግስት እና ህወሓት መካከል በደቡብ አፍሪካ ሊካሄድ የነበረው ድርድር ተራዘመ
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር በዛሬ እለት በደቡብ አፍሪካ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ቁርጠኝነቱን የገለጸው የኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን የተደራዳ ቡድን ወደ ስፍራው ስለመላኩ ይፋ አላደረገም፡፡
ፕሮፌሰር ክንደያ “አስቸኳይ ተኩስ ማቆም፣ያለተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና የኤርትራ ሃይሎች [ከትግራይ] መውጣት” ለህወሓት አንገብጋቢ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሮፌሰር ክንድያ ህወሓትን ወክለው ወደ ደቡብ አፍሪካ የተላኩት አባለት ማንነታቸውን ግልጽ አላደረጉም፡፡ ነገርግን ቀደም ሲል ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ስር ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን በገለጸበት መግለጫው ቡድኑ የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤን እንደሚያካትት መግለጹ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚስቴር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን የተደራዳሪውን ቡድን እንዲመሩ መሰየማቸውን መንግሰት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በየትኛው ቦታ እና ጊዜ ያለምንንም ቅድመ ሁኔታ ለመደራዳር ዝግጅ መሆኑንን ሲገልጽ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት የሚደራዳርባቸውን አጀንዳዎች ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡
በድጋሚ ነሀሴ አጋማሽ ላይ በተቀሰቀሰው ጦርነት የህወሓት ሃይሎች እስከ ቆቦ ድርስ መግባት እና የተወሰኑ ቦታዎች መቆጣጠር ችለው የነበረ ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት መልሶ መቆጣጠር ችሏል፡፡ ጦርነቱ አሁን የቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሽሬ፣አላማጣ እና ኮረምን መቆጣጠር መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
መንግስት ህወሓት ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በማበር የሀገር ሉአላዊነት እንዲጣስ ስላደረገ፣ በትግራይ ያሉ አየርመንገዶችንን እና የፌደራል መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ሲል መግለጹ ይታወሳል፡፡
መንግስት በትግራይ ያሉ አየርመንገዶችንን እና የፌደራል መሰረተ ልማቶችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነው ማለቱ በጦርነቱ እንደሚገፋበት አማለካች ነው፡፡