በአውሮፓ እንደ አዲስ እየተስፋፋ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት “በጣም አሳስቦኛል”- የዓለም ጤና ድርጅት
በአፋጣኝ እርምጃ ካተወሰደ በአውሮፓ እስከ ፊታችን መጋቢት 500 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሊሞቱ ይችላሉ
ዴልታ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በአውሮፓ ላለው የቫይረሱ ስርጭት ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብሏል
የዓለም ጤና ድርጅት በአውሮፓ እንደ አዲስ እየተስፋፋ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት “በጣም እንዳሳሰበው” አስታወቀ።
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት በየእለቱ ከፍተኛ የተጠቂዎችን ቁጥር ሪፖርት እያደረጉ መሆኑን ተከትሎ ነው የዓለም ጤና ድርጅት ስጋቱን የገለፀው።
የዓለም ጤና ድርጅት ቀጠናዊ ዳይሬክተር ደ/ር ሀንስ ከሉጅ እንደተናገሩት፤ ኮሮና ቫይረስ በአውሮፓ ሀገራት ውስጥ ዋነኛ የሞት መንስኤ እየሆነ ስለመምጣቱን ይናገራሉ።
የአየር ፀባይ፣ በቂ የኮሮና ቫይረስ መለካከያ ክትባ ስርጭት አለመኖር እና ዴልታ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ቫይረሱ በአውሮፓ ዳግም እንዲያገረሽ እያደረጉ ካሉ ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሾቹ ናቸው ብለዋል።
በአውሮፓ ሀገራት አፈጣኝ እርምጃ ካተወሰደ እስከ ፊታችን መጋቢት ወር 500 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሊሞቱ እንደሚችሉም ደ/ር ሀንስ ከሉጅ ተናግረዋል።
ስርጭቱን ለመግታት መፍትሄው በእጃችን ነው ያሉት ደ/ር ሀንስ፤ የሚሰጠውን የክትባት መጠን ማሳደግን ጨምሮ አዳዲስ የህብረተሰብ ጤና እርምጃዎችን መውሰድ የግድ ይላል ብለዋል።
የኮሮና ክትባትን አስገዳጅ ከማድረግ ጎን ለጎንም ሰዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) እንዲያደርጉ ማበረታታት እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።