በኮሮና እስከ 180 ሺህ የሚደረሱ የጤና ባለሙያዎች ገድሏል- የዓለም ጤና ድርጅት
የጤና ባለሙያዎች የኮሮና ክትባን እንዲያገኙ ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ዶ/ር ቴድሮስ አስታውቀዋል
በዓለም ዙሪያ ቁጥራው 135 ሚሊየን የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች እንዳሉ ይገመታል
የኮሮና ቫይረስ በዓለም ዙሪያ ቁጥራቸው ከ80 ሺህ እስከ 180 ሺህ የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎችን መግደሉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
በኮሮና ቫይረስ በቀዳሚነት እየተጠቁ ያሉት የጤና ባሉያዎች መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናረዋል።
ቫይረሱ ከአውሮፓውያኑ ታህሳስ ወር 2020 እስክ ግንት ወር 2021 ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ ከ80 ሺህ እስከ 180 ሺህ የሚደርሱ የጤና ባሙያዎችን ህይወት መንጠቁንም አስታውቀዋል።
ዶ/ር ቴድሮስ “የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ክፍፍል ፍትሃዊ አይደልም” በማለት በተቹበት ወቅት ነው ይህንን የተናገሩት።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባን የጤና ባለሙያዎች በቀዳሚነት እንዲያገኙ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በዓለም ዙሪያ ቁጥራው 135 ሚሊየን የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች እንዳሉ ይገመታል።
ከ119 ሀገራት በተሰበሰበው መረጃ መሰረት ከ5 የጤና ባለሙያዎች ውስጥ በአማካኝ ሁለቱ ሙሉ በሙሉ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መውሰዳቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ተናግረዋል።
ይህ ቁጥር ግን ከሀገር ወደ ሀገር ይለያያል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በተለይም እንደ አፍሪካ ባሉ ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ባላቸው ሀገራት ከ10 የጤና ባለሙያ ቢበዛ 1 የጤና ባለሙያ ብቻ ክትባቱን አግኝቷል ብለዋል።
ይህ ቁጥር ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም ባላቸው ሀገራት ተቃራኒ መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ በሀገራቱ በአማካኝ ከ10 የጤና ባሉያዎች 8ቱ ሙሉ በሙሉ መከተባውንም አስታውቀዋል።