የዓለም ጤና ድርጅት ድሃ ሀገራት የኮሮናቫይረስ ክትባቶችን እያጡ መሆኑን አስታወቀ
“የክትባት ኢ-ፍትሃዊነት ድሃ ሀገራት ክትባት በሚያመርቱ ሀገራት ላይ መተማመን እንደማይችሉ ያሳየ ነው” ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
እሰካሁን 5 ሚልዮን አፍሪካውያን በቫይረሱ ሲያዙ 135 ሺ ዜጎች ህይወታቸው አጥተዋል
በዓለም አቀፍ የመጋሪያ መርሃግብር መሰረት ክትባቶችን የሚቀበሉ እጅግ ብዙ ድሃ ሀገራት በቂ የክትባት መጠን ማግኘት አለመቻላቸውንም ድርጅቱ አከሏል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም “የክትባት ኢ-ፍትሃዊነት፤ በችግር ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ክትባታቸውን በሚያመርቱ ሀገሮች ላይ መተማመን እንደማይችሉ ያሳየ ነው” ብለዋል ፡፡
1.3 ቢሊዮን ህዝብ ያላትና ለአደጋ ተጋላጭ የሆነችው አፍሪካ ከዓለም ህዝብ ቁጥር 18 በመቶውን ብትይዝም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚሰጡት ክትባቶች በሙሉ 2 በመቶውን ብቻ እንደምትቀበል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
አንድ ጠብታ ያላገኙ አንዳንድ የአፍሪካ ሀገራት መኖራቸውንም ነው ሲ.ጂ.ቲ.ኤን አፍሪካ የዘገበው፡፡
ሀብታም መንግስታት ሁሉንም ህዝባቸውን ቢከተቡም፤ ክትባትን በተራቡ ሀገራት ቫይረሱ እንዲዛመት ከተፈቀደ ወረርሽኙ መከላከል እንማይቻልም የጤና ባለሞያዎች እና የዓለም መሪዎች ደጋግመው በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
የኮሮና ወረርሺኝ ከተከሰተ ወዲህ 5 ሚልዮን አፍሪካውያን በቫይረሱ ሲያዙ 135 ሺ ዜጎች ህይወታቸው አጥተዋል፡፡ የሞት መጠኑ ከሌላው ክፍለ ዓለም አንፃር ትንሽ ነው የሚባል ቢሆንም ከወረርሺኙ ስርጭት አንጻር ወደ አፍሪካ እንዳይዛመት ተሰግተዋል፡፡
ባለው የክትባት እጥረት ምክንያት 90 በመቶ የሚሆኑ የአፍሪካ ሀገራት እስከ መስከረም ወር ድረስ 10 በመቶ የሚሆነውን ህዝባቸው የመከተብ ዓለም አቀፋዊ ግብ ሊያሳኩ እንደማይችሉም ነው የዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀው፡፡
ድርጅቱ በተመድ የሚደገፈው ፕሮጀክትና ለድሃ የዓለም ሀገራት ክትባትን ለማቅረብ የተቋቋመው ኮቫክስ (COVAX) እራሱ ከባድ የክትባት እጥረት አጋጥሞታልም ነው ያለው፡፡
አሜሪካ፣እንግሊዝ እና ሌላኛው የሰባት የበለፀጉ አገራት በሚቀጥለው ሳምንት ቢያንስ 1 ቢሊዮን የመድኃኒት መጠንን ከመጪው ወርሀ ነሀሴ አንሰቶ ለተጋለጡ ሀገሮች ለማካፈል መስማማታቸው ይታወቃል፡፡:
አያሌ የዓለም ድሆች ከክትባት አምራች ሀገራት የሚጣውን ክትባት እየጠበቁና ጉዳዩን እያሳሰባቸው መሆኑንም እንዲሁ የሚታወቅ ነው፡፡