ዲዲዬር ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት አምባሳደር ሆነ
ድሮግባ በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ “የተዋጣለት ኮኮብ” መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለወጣቱ አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤንነት መጠበቅ አብረን እንሰራለን ብለዋል
ድሮግባ የዓለም ጤና ድርጅት የስፖርት እና ጤና አምባሳደር ነው የሆነው
የዓለም ጤና ድርጅት የቀድሞውን የአይቮሪኮስት እና የቼልሲ ኮኮብ ዲዲዬር ድሮግባን አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡
ድሮግባ የስፖርት እና ጤና አምባሳደር ሆኖ ነው የተሾመው፡፡
ድርጅቱ የአካላዊ እና ሌሎችንም ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጥቅም በወጣቶች ዘንድ ለማስረጽ የሚያደርገውን ጥረት በማስተዋወቅ ይደግፋል ተብሏል፡፡
“የአፍሪካ ኮኮብ” ተብሎ ለሁለት ያህል ጊዜያት የተመረጠው ድሮግባ በምዕራብ ለንደኑ እግር ኳስ ክለብ- ቼልሲ ባሰለፋቸው ድንቅ የተጫዋችነት ዓመታት ይታወቃል፡፡
በተለያዩ የጤና እና ጤናማ ህይወት፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስ፣ የወባ እና የሰላም ጉዳዮች ላይ ባለው ጉልህ ተሳትፎም ይታወቃል፡፡
በስሙ የሚጠራ የራሱን ፋውንዴሽን አቋቁሞም በትምህርት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ትናንት በስዊዘርላንድ ጄኔቭ በተካሄደ ስነ ስርዓት ነው የአፍሪካው ኮኮብ የዓለም የስፖርት እና ጤና አምባሳደር ሆኖ የተመረጠው፡፡
ድርጅቱ የሰዎችን በተለይም የወጣቶችን ጤና ለመጠበቅ ባነገበው ተልዕኮ አካል ሆኖ በመመረጡ መደሰቱን ገልጿል፡፡
“ጤና ለሁሉም አስፈላጊ ነው፤ የ2022 የዓለም ዋንጫን ጤናማ ለማድረግ በዓለም ጤና ድርጅት፣ በዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) እና በውድድሩ አዘጋጅ ኳታር መካከል ያለው ጠንካራ የቡድን ስራ ነው፤ የዚህ ስራ አካል በመሆኔ ተደስቻለሁ” ሲልም ነው ድሮግባ የገለጸው፡፡
“አፍሪካዊ ብሄራዊ ቡድን በቅርቡ የዓለም ዋንጫን ማንሳት አለበት” አዲሱ የካፍ ፕሬዝደንት
ድሮግባ በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ “የተዋጣለት ኮኮብ” መሆኑን የተናገሩት የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤንነት መጠበቅ ያግዘናል ብለዋል፡፡
ዲዲዬር ከቀድሞው የብራዚል ኮኮብ አሊሰን ቤከር፣ ከቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ጎርደን ብራውን እና ሌሎች የድርጅቱ አምባሳደሮች እና ታዋቂ ሰዎች ጋር በመሆን ነው የሚሰራው፡፡