የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በኢትዮጵያ የኮሮና ስርጭት አስጊ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል
በኢትዮጵያ ያለው የበኮቪድ 19 የመያዝ ምጣኔ አስጊ በሆነ ደረጃ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አስታውቋል።
ባሳለፍነው ሳምንት ባለው መረጃ መሰረት በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተያዙ ግለሰቦች በ 2 በመቶ ያህል መጨመር ያሳየ ሲሆን፤ በአፍሪካም በዚሁ ሳምንት በ10 በመቶ በኮቪድ-19 ቫይረስ የሚያዙ ግለሰቦች ጭማሪ ማሳየቱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
በኢትዮጵያም በኮቪድ 19 ቫይረስ የመሰራጨት አቅሙን ጨምሮ አስጊ በሆነ ደረጃ በ12.80 በመቶ በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ መጨመሩን ነው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት መረጃ የሚያመለክተው።
መጋቢት 1 እና 2፣ 2013ዓ.ም የወጡ ሪፖርቶችን ሲታዩ፡ 01/2013 በኢትዮጵያ 7 ሺህ 819 ግለሰቦች የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 543 ግለሰቦች የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡
ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ ወይም 20 በመቶ የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡መጋቢት 2 2013 በተደረገው ምርመራ እንደ ሀገር በሽታው የመገኘት ምጣኔ 19 በመቶ መደረሱን የወጣው ሪፖርት ያመለክታል።
በከተሞች ደረጃ በሽታው የመግኘት ዕድል በጣም ከፍተኛ የሆነባቸው ተብለው የተለዩትም፣ ሐዋሳ - 42 በመቶ፣ድሬዳዋ - 27 በመቶ እና በአሶሳ - 23.5 በመቶ ናቸው፡፡
4. አዲስ አበባ - 20 በመቶ መሆናቸውንም የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት እና ከቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲከል ኮሌጅ ያወጡት መረጃ ያመለክታል።
በአሁኑ ወቅት በኮሮና የተጠቁ 171ሺ 210 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 2483 ህይወታቸው አልፏል፡፡ 428 በጽኑ ህሙማን መቆያ ውስጥ ገብተዋል፡፡