ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ 19 ክትባት በኮቫክስ በኩል መረከቧ ይታወሳል
ክትባቱ በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እፎይታ ጤና ጣቢያ በዛሬው እለት በይፋ መሰጠት ተጀምሯል፡፡
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ክትባት መርሃ ግብሩን ያስጀመሩ ሲሆን፥ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከገባ ጀምሮ በሽታውን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ግንባር ቀደም ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
የኮቪድ -19 ክትባትም በቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ የገለፁት ወይዘሮ አዳነች ህብረተሰቡም ክትባቱ እስኪደርሳቸው ድርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ የፕሬስ ሰክሪታሪያትመረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ በበኩላቸው በኮቫክስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኮቪድ-19 ክትባት በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች፣ በእድሜና ለበሽታው ተጋላጭ ጤና ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሠብ ክፍሎች እንደሚሠጥ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በመጀመሪያ ዙር 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ 19 ክትባት በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት በኩል መረከቧ ይታወሳል።