ልዩልዩ
የኮሮና ክትባት በአማራ ክልል ደረጃ በባህርዳር ፈለገህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል መሰጠት ተጀመረ
በሀገር አቀፈ በተሰጠው ኮታ 108 ሺህ ዶዝ ክትባት ለአማራ ክልል ተሰጥቷል
የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ ከፍተኛ ሥራ ሃላፊዎችና የጤና ባለሙያዎች ተከትበዋል
የክትባቱ ማሥጀመሪያ ላይ የክልሉ የክልሉ ርዕስ መስተዳድረ አቶ አገኘሁ ተሻገርና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተተገኝተዋል።
የአማራ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ፈነታ ማንደፍሮ፣ የጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ ፣ሌሎች አመራሮች እና የጤና ባለሞያዎችን ክትባቱን ተከትበዋል።
በሀገር አቀፈ በተሰጠው ኮታ መሰረት 108 ሺህ ዶዝ ክትባት ለአማራ ክልል መሰጠቱን የክልሉ የህበረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ በክትባቱ ወቅት ገልጸዋል።
ክትባቱ በሁለት ዙር የሚሰጥ መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተር አቶ በላይ በዛብህ፤ ሁለተኛ ዙር ክትባትም በቀጣይ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።