የተከሰከሰው የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ከፍተኛ ባለስልጣናትን አስቸጋሪ ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት ከጥቃት የሚያድን ነበር ተባለ
በግጭቱ የ12ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበሩ እና በሀገራዊ ቀውስ ጊዜ የፔንታጐን ባለስልጣናትን ጨምሮ ከጥቃት የማዳን ኃላፊነት ያለባቸው ሶስት ወታደሮች ሞተዋል
በግጭቱ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ አራት ወታደሮችን ጨምሮ ከ60 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል
ከመገደኞች አውሮፕላን ጋር ተጋጭቶ የተከሰከሰው የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር በአስቸጋሪ ሁኔታ ወቅት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከጥቃት ለማዳን በሚያስችል ልምምድ ላይ እንደነበር ተገልጿል።
ባለፈው ረቡዕ እለት በዋሽንግተን ከመንገደኞች አውሮፕላን ጋር ተጋጭቶ የተከሰከሰው የአሜሪካ ጦር ብላክ ሀውክ ሄሊኮፕተር አስቸጋሪ ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ለማሸሽ በሚያስችል ልምምድ ላይ እንደነበር ሮይተርስ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።
"መንግስት ማስቀጠል" እና "ዘመቻ ማስቀጠል" በሚል ስያሜ የሚታወቀው ተልእኮ የሚካሄደው የአሜሪካን መንግስት የማድረግ አቅም ለማስጠበቅ ነው።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ፔቴ ሀግሴዝ የብላክ ሀውክ ቡድን በተለመደ አመታዊ ልምምድ ተልእኮ ላይ እንደነበሩ ይፋ አድርገዋል። እንዲህ አይነት በረራዎች ብዙ ጊዜ ይፋ የሚደረጉ አይደሉም።
በግጭቱ የ12ኛ ክፍለ ጦር አባል የነበሩ እና በሀገራዊ ቀውስ ጊዜ የፔንታጐን ባለስልጣናትን ጨምሮ ከጥቃት የማዳን ኃላፊነት ያለባቸው ሶስት ወታደሮች ተገድለዋል። በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ የነበሩ 64 ሰዎች በግጭቱ ህይወታቸው አልፏል።
የብላክ ሀውክ ቡድን 'ጉግለርስ' ወይም በምሽት በማየት በሚያስችል መሳሪያ በመጠቀም የልምምድ በረራቸውን መስመር 4 በመባል በሚታወቀው በፖቶማክ ወንዝ ላይ እያበረሩ ነበር።
ጦሩ በረራ በሚበዛበት ኤየርፖርት ለምን ይህን በረራ አደረገ የሚል ጥያቄ እየቀረበበት ይገኛል።
"የተወሰኑት ተልእኮዎቻቸን በዚህ ቦታ መጥፎ አደጋ ቢያጋጥም መከላከያ ሚኒስቴርን ለመደገፍ የሚያስችሉ ናቸው፤ ከፍተኛ ባለስልጣኖቻችን ማዳን አለብን"ሲሉ የአሜሪካ ጦር የበረራ ዋና አዛዥ ጆናታን ኮዚኦል ተናግረዋል።
በቅርብ ጊዜ የአሜሪካ መንግስት የአስቸጋሪ ሁኔታ ተልእኮውን ያንቀሳቀሰው የአልቃ ኢዳ አውሮፕላን ጠላፊዎች በ2001 በኒው ዮርክ ከተማ የሚገኙትን መንትያ የአለም ንግድ ማዕከል ህንጻዎችን በገጩበትና 3000 ሰዎች ህይወታቸውን እንዲያጡ ባደረጉበት ወቅት ነበር።
"ይህ ክፍለ ጦር የተወሰኑ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስለጣናትን ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ መደበቂያ በማሸሽ እርዳታ አድርጓል"ሲሉ በጥቃቱ ወቅት በረራ ያደረጉ የቀድሞ የጦሩ የበረራ ሰራተኛ ብራድሊ ቦውማን ለሮይተርስ ተናግረዋል።
ቦውን ጥቃቱ በተፈጸመበት ምሽት የወቅቱን ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ፖል ውልፈቀውትዝን ከአንድ ቦታ በማንሳት ወደ ፔንታጎን አድርሷል።
በግጭቱ በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ አራት ወታደሮችን ጨምሮ ከ60 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።