በ2006 የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ጎሉን ያስቆጠረው ሮናለድ ለሀገሩ 117 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል
ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአስምትተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች ላይ ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ተጫዋች በመሆን አዲስ ክብረወስን በእጅ ማስገባት ችሏል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ባለ ክብረወሰን ያደረገውን ጎሉን በዛሬው እለት በጋና ላይ ማስቆጠር ችሏል።
ሀገሩ ፖርቹጋልን በመወከል በኳታር የ2022 የዓለም ዋንጫ ላይ እየተሳተፈ ያለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ እስካነ ለሀገሩ በዓለም ዋንጫ ላይ ስምንት ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ክርስቲያ ሮናልዶ የመጀመሪያ የዓለ፣ የዓለም ዋጫ ጎሉን ከመረብ ማሳረፍ የቻለው ለሁለተኛ ጊዜ በተሳተፈበት በ2006 በጀርመን በተካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ በ80ኛ ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ነበር።
ጎሉ ለሮናድ በሀገሩ አዲስ ክብረወሰን እንዲያስመዘግብ ያደረገገ ሲሆን፤ በወቅቱ 21 ዓመት የነበረው ሮናለድ በትንሽ እድሜ ለፖርቹጋል ጎል ያስቆጠረ የመጀመሪያ ተጫዋች አድርጎታል።
ክርቲያኖ ሮናድ ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ ለሀገሩ ፖርቹጋል እስካሁን ድረስ 118 ጎሎችን ከመረብ ማሳረፍ መቻሉም ነው ተገለጸው።
ከፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ጋር ስሙ እኩል የሚነሳው ክርስቲያኖ ሮናልዶ የኳታር 2022 የዓለም ዋንጫ የመጨረሻው የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ እንደሚሆን ተገምቷል።
በመጨረሻ የአለም ዋንጫ ተሳትፎው የተሻለ ውጤታማ እንዲሆን የሚመኙለት የስፖርት ወዳጆች በርካታ ናቸው።
የአራት ጊዜ ባሎንዶር አሸናፊው፤ ከ800 በላይ ጎሎችን በማስቆጠር ክብረወሰን መያዙም ይታወቃል።