ስፖርት
የአሜሪካ ፍ/ቤት በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ የቀረበው ክስ ውድቅ አደረገ
በ2010 የክርስቲያኖ ሮናልዶ ጠበቆች 375 ሺህ ፓወንድ በመክፈል ካትሪን ክሱን እንድታቋርጥ ማድረጋቸው ይታወሳል
ካትሪን ማዮርጋ የምትባል እንስት በ 2009 ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወሲባዊ ጥቃት ፈጽሞብኛል በማለት መስርታ ነበር
የአሜሪካ ፍርድ ቤት የማንችስተር ዩናይትድ እና የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች በሆነው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ቀርቦ የነበረው የወሲባዊ ጥቃት ክስ ውድቅ አደረገ።
ክሱን ውድቅ ያደረገው በአሜሪካ የላስ ቬጋስ ፍርድ ቤት ነው ።
ካትሪን ማዮርጋ የምትባል እንስት በ 2009 ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወሲባዊ ጥቃት እንደፈጸመባት በመግለፅ ክስ መስርታ ነበር።
የእንስቷ ጠበቆች በህጋዊ መንገድ ያልተገኙ መረጃዎችን ለፍርድ ቤት አቅርበዋል ተብሏል። በዚህም መሠረት በፖርቹጋላዊው ተጫዋች ላይ የቀረበው ክሱ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ተገልጿል ።
በ2010 የክርስቲያኖ ሮናልዶ ጠበቆች 375 ሺህ ፓወንድ በመክፈል ካትሪን ማዮርጋ ክሱን እንድታቋርጥ ማድረጋቸው ይታወሳል።
በድጋሚ እ.አ.አ በ 2019 ካትሪን ማዮርጋ ክስ አቅርባ የነበረ ሲሆን በላስ ቬጋስ ፍርድ ቤት ግን ክሷን ውድቅ አድርጎባታል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግር ኳስ ህይወቱ 815 ግቦችን ሲያስቆጥር ተቀናቃኙ ሊኦኔል ሜሲ ደግሞ 769 ግቦችን አስቆጥሯል።