መኖሪያው ቅንጡ እና ለእይታ የተመቸ ነበር ተብሏል
“የበጎች ድምጽ ረበሸኝ”ያለው አዲሱ የማንችስተር ዩናየትዱ ፈራሚ ክርስቲያኖ ሮናልዶ መኖሪያ ቤቱን ቀየረ፡፡
ክርስቲያኑ ከአንድ ወር በፊት መኖር የጀመበረበትን ቤት ነው የለቀቀው፡፡
ፖርቹጋላዊው አጥቂ ከ12 ዓመታት በኋላ ዩናይትድን መልሶ መቀላቀሉ ይታወሳል።
ተጫዋቹ ወደ ማንችስተር ከተመለሰ በኋላ መኖሪያውን በከተማው በሚገኝ አንድ ቅንጡ ቪላ አድርጎ ከቤተሰቡ ጋር በመኖር ላይ ነበር።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብዙ እግር ኳስ ቡድኖች የሌሏቸው ዋንጫዎች አሉት
6 ሚሊዮን ፓውንድ ዋጋ እንዳለው የተነገረለት ቪላው ሜዳ እና በደን የሚተሸፈነ ለመኖሪያ ምቹ እንደነበር ተገልጿል።
ሆኖም ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ በቅንጡ መኖሪያ ቤቱ የተነሳቸውን ፎቶዎች ይለቅ የነበረው ሮናልዶ “ረበሸኝ” ባለው የበጎች ድምጽ ምክንያት መተኛት እንዳልቻለ ገልጿል።
በዚህ ተገዶ ቅንጡውን መኖሪያ መልቀቁንም ነው ዘ ሰን ጋዜጣ የዘገበው፡፡