በቻይና በኮሮና ቫይረስ በአንድ ቀን ብቻ 242 ሰዎች ሞቱ
በቻይና በኮሮና ቫይረስ በአንድ ቀን ብቻ 242 ሰዎች ሞቱ
በቻይና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በተቀሰቀባት ሁቤ ግዛት ውስጥ በአንድ ቀን ብቻ ሪኮርድ የሰበረ 242 ሞት መመዝገቡን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ሰኞ በአንድ ቀን 103 ሰዎች በዚሁ ግዛት ሲሞቱ ከፍተኛ የሞት ቁጥር ተብሎ ተመዝግቦ ነበር፡፡ የሀገሪቱ የጤና ኮሚሽን እንዳስታወቀው እስካሁን ድረስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ብቻ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,310 ከፍ ብሏል፡፡
የወረርሽኙ መነሻ በሆችው በሁቤ ግዛት 14, 840 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ያስታወቀው ኮሚሽኑ አሮጌ ያለውን መረጃና የተጠረጠሩ ጉዳዮችን አሻሽላለሁ ብሏል፡፡
በቅርብ የተጠቀሰው የሞት ቁጥር ህክምና ተደርጎላቸው የሞቱትን 100 ሰዎች ይጨምራል፡፡
የመንግሰት መገናኛ ብዙሀን ባለፈው እንደዘገቡት በሁቤ ግዛት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመለየት በኮምፑተር የታገዘ ምርመራ ማደራጀት መጀመሩን የዘገቡ ሲሆን፣ይህም ሆስፒታሎችን ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች በቀላሉ ለመለየት እንደሚያስችላቸው ተገልጿል፡፡
እስካሁን በግዛቷ 48,206 በቫይረሱ መያዛቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡
ቻይና በሁቤ ግዛት ከተከሰተው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ጋር በተያያዘ በርካታ የግዛቷን አመራሮች ከስልጣን ከማንሳት ጀምሮ ሌሎች በርካት እርምጃዎችን ወስዳለች፡፡