የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ትናንት በ97 ጨምሮ 1,115 ደረሰ፡፡
የኮሮና ቫይረስ ሟቾች ትናንት በ97 ጨምሮ 1,115 ደረሰ፡፡
በኮሮና ቫይረስ ከሞቱት 1,115 ሰዎች መካከል 1,114ቱ ቻይናውያን (አንድ የሆንግ ኮንግ ነዋሪን ጨምሮ) ሲሆኑ አንዱ ፊሊፒናዊ ነው፡፡
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ደግሞ ትናንት ከነበረው በ2,029 ጨምሮ 45,127 ደርሷል፡፡ ከነዚህም 44,730 ሰዎች ቻይናውያን ሲሆኑ የተቀሩት 397 ሰዎች የሌሎች ሀገራት ዜጎች ናቸው፡፡
የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር እኤአ ከ የካቲት 4 እስከ 11(ባለፈው አንድ ሳምንት) በ48.2 በመቶ መቀነሱን የሀገሪቱ ጤና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ 4,740 ሰዎች ከቫይረሱ ድነው ከሆስፒታል መውጣታቸውም በሲጂቲኤን ዘገባ ተካቷል፡፡
የኮሮና ቫይረስ ክትባት በ18 ወራት ውስጥ ሊገኝ እንደሚችል የጠቆሙት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም በመሆኑም ክትባቱን የማግኘቱ ነገር ጊዜ ስለሚወስድ ባለን አቅም ሁሉ ስርጭቱን ለመግታት መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡
የተለያዩ ሳይንቲስቶች፣ ሀገራት እና ኩባንያዎች ለቫይረሱ መድሀኒት ለማግኘት በሩጫ ላይ ቢሆኑም ይህ ግን ረዥም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ነው ዶ/ር ቴድሮስ የጠቆሙት፡፡