ለአዲሱ ገንዘብ ህትመት ከ3.7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሆኗል፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ
አሁን በገበያ ላይ ያለው ገንዘብ በ3 ወራት ውስጥ ይቀየራል፡ ብሔራዊ ባንክ
አሮጊው በአዲሱ ብር በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እስከሚቀየር ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ስራ ላይ እንደሚውሉ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ
አሮጊው በአዲሱ ብር በ3 ወር ጊዜ ውስጥ እስከሚቀየር ድረስ ሁለቱም ጎን ለጎን ስራ ላይ እንደሚውሉ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ
ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ይፋ መደረጉን አድርጋለች፡፡
አሁን በገበያ ውስጥ ያለውን ገንዘብ በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚቀየር የብሔራዊ ባንክ ገዥው ዶ/ር ይናገር ደሴ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ይናገር እንደገለጹት ገንዘቡን የመቀየር ሂደቱ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡
አብዛኛው የመቀየር ስራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይ የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ-ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ዝግጅት መደረጉ ተነግሯል፡፡
አብዛኛው የሕትመት ሥራ ተገባዶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ግምጃ ቤት እንደሚገኝ እና የስርጭት ስርዓት እና ዕቅድ ተዘጋጅቶ በሚመለከታቸው አካላት አማካኝነት የሚተገበር እንደሚሆንም ዶ/ር ይናገር ገልጸዋል፡፡ ይህንን የሥርጭት ሂደት በበላይነት የሚያስተባብር ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት እንደሚቋቋምም ነው የተገለጸው፡፡
አሁን ላይ ግን አሮጌውንና አዲሱን የብር ኖት ጎን ለጎን መጠቀም እንደሚቻልም የብሔራዊ ባንክ ገዥው አስታውቀዋል፡፡
ለአዲሱ የገንዘብ ህትመት 3 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የገንዘብ ኖቶችን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
በጎረቤት ሀገራት የሚገኝ የኢትዮጵያ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት እንዳይገባ መከላከያ ሰራዊት ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ የግል ባንኮችም ሀሰተኛ የብር ኖቶችን እንዳይቀበሉና ይህንን በሚያደርጉ ላይ ባንኩን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡