ከወር በፊት ፍንዳታ በተከሰተባት በቤሩቷ የወደብ ከተማ እሳት ተነሳ
በእሳቱ ምክንያት የሚከሰት ሌላ የፍንዳታ ስጋት አለመኖሩን የሌባኖስ ቀይመስቀል አስታውቋል
እሳቱ የተነሳው በቤሩቷ የወደብ ከተማ በሚገኝ የነዳጅና የጎማ እቃቤት ላይ መሆኑ ተገልጿል
እሳቱ የተነሳው በቤሩቷ የወደብ ከተማ በሚገኝ የነዳጅና የጎማ እቃቤት ላይ መሆኑ ተገልጿል
በከወር በፊት ከፍተኛ ፍንዳታ ተከስቶ መጠነ ሰፊ ጉዳት ባደረሰበት በቤሪቷ የወደብ ከተማ የነዳጅና የጎማ እቃቤት ላይ ከፍተኛ እሳት መነሳቱ የተዘገበ ሲሆን እስካሁን በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ጦር እቃ ቤቱ እንዴት እንደተቃጠለ ወዲያውኑ ግልጽ ባያደርግም እሳቱን በቀጥጥር ስር ለማዋል ሄሊኮፕተሮችን ወደ ቦታው ልኳል፡፡ በቴሌቪዥን በተለቀቀ ምስል ማየት እንደተቻለው ከሆነ ሄሊኮፕተሮቹ እሳቱን ለማጥፋት ውሃ ሲያርከፈክፉ ታይተዋል፡፡
ይህ እሳት ከወር በፊት በነበረው ፍንዳታ የስነልቦና ጫና ውስጥ በነበረችው ከተማ ላይ ከፍተኛ ጭስ አስከትሏል፡፡ በወቅቱ በነበረው ፍንዳታ 190 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውና 6ሺ ሰዎች ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል፡፡
የሊባኖስ የቀይመስቀል ኃላፊ ጎርጅ ኬታነህ በእሳቱ ምክንያት የሚከሰት ሌላ የፍንዳታ ስጋት አለመኖሩንና የሰው ጉዳት አለመድረሱንም ገልጸዋል፡፡ በጭሱ ምክንያት ለመተንፈስ የተቸገሩ ሰዎች መኖራቸው ተጠቅሷል፡፡
ፍንዳታው የተከሰተው ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ በወደብ በተከማቸ አሞኒየም ናይትሬት ምክንያት ነው ተብሏል፡፡