ኢራን ኮሮና እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ለ15 ሚሊዮን ተማሪዎቿ ት/ቤቶችን ከፈተች
በኢራን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስካሁን ከ22ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል
በመካከለኛው ምስራቅ በከፍተኛ ደረጃ በኮሮና በተጠቃችው ኢራን ት/ቤቶች ከ 7 ወራት በኃላ ተከፈቱ
በመካከለኛው ምስራቅ በከፍተኛ ደረጃ በኮሮና በተጠቃችው ኢራን ት/ቤቶች ከ 7 ወራት በኃላ ተከፈቱ
በኢራን ምንም እንኳን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እተባባሰ ቢሄድም ሀገሪቱ ለ15 ሚሊዮን ተማሪዎቿ ትምህርት ቤቶችን ከተዘጉ ከ7 ወራት በኋላ ልትከፍት ነው፡፡
የትምህርት ቤቶቹን መከፈት የሚከታተሉት ፕሬዘዳንት ሀሰን ሮሀኒ በቀጥታ በቴሌቪዝን በተላለፈ ስርጭት ባደረጉት ንግግር “በዚህ አመት ተማሪዎቻችን በሚመለከት ከፍተኛ ሃላፊነት አለብን” ብለዋል፡፡ ትምህርትና ጤና እኩል አስፈላጊ ናቸው ያሉት ፕሬዘዳንቱ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ እንደማይገደዱ ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ቅዳሜ የእምነት ትምህርት ቤቶች 50ሺ ለሚሆኑ ተማሪዎች መከፈታቸውን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡በመካለኛው ምስራቅ በከፍተኛ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ በተጠቃችው ኢራን የትምህርት ቤቶችና የዩኒቨርሲቲዎች በድጋሚ መከፈት የሚዲያ ሰዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
በመንግስት የተሾሙት የኢራን ሜዲካል ካውንስል ኃላፊ ዶክተር መሀመድ ሬዛ ዛፋርጋንዲ ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ በጻፉት መልእክት የትምህርት ቤቶች በድንገት መከፈት በጤና ባለሙያዎች ላይ ጫና እንደሚያሳድር ጥርጥር እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ዛፋርጋንዲ እንደገለጹት ሀገሪቱ በወረርሽኙ ስትመታ በመጀመሪያ የተጠቁት ትምህርት ቤቶች ነበሩ ብለዋል፡፡
በኢራን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት እስካሁን 22ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ384ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ተጠቅተዋል፡፡