በቱር ደ ፍራንስ ውድድር ላይ ሚስቱን የሳመው ሰው ቅጣት ተጣለበት
ተወዳዳሪው ድርጊቱን የፈተመው ውድድሩን ሊጨርስ ጥቂት ርቀት ሲቀረው ሚስቱን እና ልጁን በማየቱ ደስ ብሎት መሆኑን ተናግሯል
አወዳደሪው አካል ግለሰቡ የውድድሩን ህግ ጥሷል በሚል ነው ቅጣት የጣለበት
በቱር ደ ፍራንስ ውድድር ላይ ሚስቱን የሳመው ሰው ቅጣት ተጣለበት፡፡
ጁሌን በርናርድ ፈረንሳዊ ሲሆን ከሰሞኑ በተካሄደው የቱር ደ ፍራንስ የሳይክር ውድድር ላይ ከተሳተፉት ስፖርተኞች መካከል አንዱ ነው፡፡
ይህ ስፖርተኛ በውድድሩ ሰባተኛ ዙር ማጠናቀቂያ ላይ ሚስቱን ስሟል የተባለ ሲሆን በዚህም ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጾ ነበር፡፡
የውድድሩ አዘጋጅ አካል ተወዳዳሪው ብስክሌተኛ የውድድሩን ህግ እና ደንብ በመጣስ ጥፋት ሰርቷል በሚል ቅጣ እንደሚጠብቀው ከዚህ በፊት ገልጾ ነበር፡፡
ተወዳዳሪው በርናርድ በበኩሉ ጥፋት ማጥፋቱን እና የሰራው ስራም የውድድሩን ክብር የሚነካ መሆኑን አረዳለሁ የሚጠልብኝንም ቅጣ በጸጋ እቀበላለሁ ሲል ተናግሮም ነበር፡፡
በወቅቱ ባልጠበቅሁት ሁኔታ ሚስቴ እና ልጄ እኔን ሊያበረታቱኝ ወደ ስፍራው እንደመጡ ሳይ ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም ሲል በርናርድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ጽፏል፡፡
በዚህም መሰረት ይህ ስፖርተኛ 223 ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት ሲገለጽ ላጠፋው ጥፋት ይቅርታ እንዲደረግለት ጠይቋል፡፡
ተወዳጅ የሳይክል ውድድር የሆነው ቱር ደ ፍራንስ ለየት ያለ ህግ ያለው ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት በስፖርተኞች ላይ አደጋ እንዲደርስ ምክንት ሆነሻል ያላትን አንድ ተመልካች 1 ሺህ 300 ዶላር ቅጣት ማስከፈሉ ይታወሳል፡፡