የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት መልኩን እየቀያየረ ሶስተኛ ዓመቱን ይዟል
ሩሲያ ወደ ዩክሬን የገቡ የፈረንሳይ ወታደሮችን እንደምትመታ ዛተች፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከአንድ ወር በፊት ወታደሮችን ወደ ዩክሬን ለመላክ ማሰባቸውን ተናግረው ነበር፡፡
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ላይ አክለውም ሩሲያ ለአውሮፓ ስጋት መሆኗን በዩክሬን እና ሌሎች ሀገራትም የፈረንሳይን ጥቅም እየጎዳች ነው ብለዋል፡፡
ከሰሞኑ የፈረንሳይ ወታደሮች ዩክሬንን ለመርዳት በሚል ወደ ኪቭ እንደመጡ የተገለጸ ሲሆን ሩሲያ ለዚህ ምላሽ ሰጥታለች፡፡
የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛራኮቫ እንዳሉት በዩክሬን ያሉ የፈረንሳይ ወታደሮች ኢላማ ይሆናሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዛራኮቫ አክለውም “ፈረንሳይን ማበሳጨት አለብን፣ በኪቭ የሚገኙ የፈረንሳይ እግረኛ ወታደሮችን የመምታት ህጋዊ መብት አለን” ሲሉም አክለዋል፡፡
የሩሲያ ወታደሮች የአሜሪካ ጦር ወደሚኖርበት የጦር ሰፈር ገቡ
ባለፉት ጊዜያት የፈረንሳይ ዜግነት ያላቸው ቅጥረኛ ወታደሮች ለዩክሬን ሲዋጉ የተገደሉ በርካታ ሰዎች እእንዳሉ እናውቃለን ያሉት ቃል አቀባይዋ የአሁኖቹ ወታደሮችም በጦርነት ቀጠና ውስጥ ከተገኙ ይመታሉም ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን ከሰሞኑ የፈረንሳይ፣ ብሪታንያ እና አሜሪካ ተጽዕኖ እየጨመረ ነው በሚል ጦራቸው የታክቲካል ኑክሌር ጦር ልምምድ እንዲያደርግ ማዘዛቸው ይታወሳል፡፡
ጀርመን እና ሜሪካን ጨምሮ በርካታ ሀገራት እግረኛ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን መላክን ተቃውመው በይፋ የተናገሩ ሲሆን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶ በበኩሉ ወታደሮችን ወደ ዩክሬን መላክ የኑክሌር ጦርነት እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል የፈረንሳይን ውሳኔ ተቃውሟል።