በቱርክ የደረሰ ርዕደ መሬት ያስከተለው ውድመት
በአደጋው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት አልፏል
በቱርክ እና ሶሪያ በርዕደ መሬት 7 ነጥብ 8 የሆነ ርዕደ መሬት ተከስቷል
በቱርክ እና ሶሪያ በርዕደ መሬት 7 ነጥብ 8 የሆነ ርዕደ መሬት ተከስቷል።
በአደጋው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ ምክንያት አልፏል፤በርካቶች የደረሱበት አልታወቀም።
ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በትናንትናው እለት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎችን ለማሰብ ነው የሀዘን አዋጁን ያወጁት።
የቱርክ ባንዲራ እስከ ቀጣዩ ሳምንት ድረስ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል።
በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 8 ሆኖ የተመዘገበው ርዕደ መሬት በቱርክ ብቻ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፤ የነፍስ አድን ስራው ባለመጠናቀቁም የሟቾቹ ቁጥር እንደሚያሻቅብ ይጠበቃል።
በአደጋው ከ2 ሺህ 800 በላይ ህንጻዎች መፈራረሳቸውን ያነሱት ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን፥ ይህም ከፈረንጆቹ 1999 ወዲህ የደረሰ አሰቃቂ አደጋ ያደርገዋል ብለዋል።
ኤርዶሃን ከ9 ሺህ በላይ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ተሰማርተው የነፍስ አድን ስራዎችን መከወናችን ስለመቀጠላቸውም ተናግረዋል።