ስብ ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ በሰው ጤና ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች
ስብ ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ በጤና ላይ መጠነሰፊ ጉዳት ያስከትላል
የተመጣጠነ ምግብ እና ውስን ስብ መመገብ ለሰውነት ጤና በጣም ወሳኝ ነው
ስብ ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ በሰው ጤና ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች
ስብ ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ በጤና ላይ መጠነሰፊ ጉዳት ያስከትላል።
ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።
1) ከፍተኛ ስብ ያለባቸው ምግቦች እና ትራንስ ፋትስ የኤልዲኤል ኮሌስትሮል መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፤ ይህም የልብ ህመም እና የስትሮክ ተጋላጭነትን ይጨምራል።
2) ክብደት መጨመር እና ከመጠን ያለፈ ውፍረት
ስብነክ ምግቦች የካሎሪ ክምችታቸው ከፍተኛ ስለሚሆን በተደጋጋሚ ከተመገብናቸው ከመጠን ላለፈ ውፍረት እና እንደ ዲያቤትስ ወይም የስኳር በሽታ አይነት የጤና ችግር ያስከትላል።
3) የምግብ አለመፈጨት
ከፍተኛ የስብ ክምችት ያላቸው ምግቦች በቀላሉ ስለማይፈጩ የተቅማጥ በሽታን ያስከትላሉ።
4) ስብን አብዝቶ መመገብ የጉበት በሽታ ያመጣል። በጊዜ ሂደትም ጉበት ስራውን እንዲያቆም ሊያደርግ ይችላል።
5) የምግብ አለመመጣጠን
ከፍተኛ ስብ ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ፣ ሌሎች ለሰውነታችን አስፈላጊ ንጥረ ምግቦችን እንዲያጥረን ሊያደረግ ይችላል።
6) የሰውነት ሽፍታ
የተወሰኑ ስቦች በተለይም ትራንስ ፋትስ በሰውነታችን ላይ ትናንሽ እብጠቶች ወይም ሽፍታ እንዲከሰት ያደርጋል። ይህም የተለያዩ የጤና ችግሮችን ያባብሳል።
የተመጣጠነ ምግብ እና ውስን ስብ መመገብ ለሰውነት ጤና በጣም ወሳኝ ነው።