ኢኮኖሚ
ዳቮስ 2024.. በዓለም ኢኮኖሚ የጠፋውን መተማመን መፈልግን አላማ ያደረገ ጉባዔ
54ኛው የዳቮስ ግሎባል ፎረም ከዛሬ ከጥር 7 እስከ ጥር 11 ይካሄዳል
ጉባዔው መካለኛው ምስራቅና የጋዛ ጦርነትና የአየር ንብረት ለውጥና የኮፕ28 ስኬቶች ይገመግማል
የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም ዓመታዊ ስብሰባውን በስዊዘርላንድ ዳቮስ ከዛሬ ጀምሮ እንደሚያካሂድ ይጠበቃል።
በ54ኛው የዳቮስ ግሎባል ፎረም100 መንግስታትን እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን የሚወክሉ 2,500 ተሳታፊዎች እንዲሁም 1000 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ።
“መተማመንን እንደገና መገንባት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባዔው፤ መካለኛው ምስራቅና የጋዛ ጦርነት፣ እድገትን እና ስራዎችን መፍጠር፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ንዲሁም የኮፕ28 ስኬቶችን አጀንዳ አድርጓል።