የዓለማችን ሀገራት ድምር ብድር 88 ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ
ኮሮና ቫይረስ እና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ሀገራት ተጨማሪ ብድሮችን እንዲበደሩ ያደረጉ ምክንያቶች ናቸው
መንግስታት ያለባቸውን ብድር ለመክፈል የሚወስዷቸው እርምጃዎች ኢኮኖሚውን ሊጎዱ እንደሚችል ተገልጿል
የዓለማችን ሀገራት ድምር ብድር 88 ትሪሊዮን ዶላር ደረሰ፡፡
የዓለማችን ሀገራት መሪዎች በጋራ ችግሮቻቸው ዙሪያ ለመወያየት ወደ ስዊዘርላንዷ ዳቮስ እያመሩ ሲሆን በመድረኩ ላይ በዋና ዋና ችግሮች ዙሪያ እንደሚመክሩ ይጠበቃል፡፡
ባለሙያዎች አስቀድመው ወደ ቦታው ያመሩ ሲሆን ዋና ዋና የዓለማችን ችግሮች በሚባሉ ጉዳዮች ዙሪያ መፍትሔ ያሏቸውን ሀሳቦች መሪዎች እንዲወስኑባቸው በማመቻቸት ላይ ናቸው፡፡
የዓለማችን ሀገራት ከገጠማቸው ችግሮች ዙሪያ ዋነኛው የሀገራት ብድር መጠን መጨመር ዋነኛው ሲሆን የብድር መጠን 88 ትሪሊዮን ደርሷል፡፡
በኮሮና ቫይረስ ወቅት ሀገራት ዜጎቻቸውን ለመጠበቅ የወሰዷቸው እርምጃዎች የመንግስታትን ወጪ እንዲጨምር እንዳደረገም ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ ብድር መክፈል ከማይችሉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ተካተተች
በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በተከሰተው የነዳጅ እና ምግብ ዋጋ መናር ሌላኛው የመንግስታትን ወጪ ያናረ ጉዳይ ሲሆን ተጨማሪ ግጭቶችም ሀገራት ተጨማሪ ብድር እንዲወስዱ አድርጓልም ተብሏል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ዓለማችን ተጨማሪ ጦርነት በቀይ ባህር አካባቢ ማስተናገዱን ተከትሎ የነዳጅ እና ምግብ ዋጋ እየጨመረ ሲሆን ለዓለም ኢኮኖሚ ሌላኛው ፈተና እየሆነ ይገኛል፡፡
በተያዘው ዓመትም አሜሪካ፣ ብሪታንያ እና ሩሲያን ጨምሮ ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪ እና በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ተሳትፎ የሚያደርጉ ሀገራት ምርጫ ያደርጋሉ መባሉ ወደ ስልጣን የሚመጡ መንግስታት የሚወስኗቸው አዳዲስ ውሳኔዎች ኢኮኖሚውን ሊጎዱ እንደሚችሉ ተሰግቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የበይነ መረብ ደህንነት፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ለዓለም ኢኮኖሚ ፈተና ይሆናሉ ተብለው የተለዩ ሲሆን ሀገራት ይህን ችግር ለመፍታት ተጨማሪ ውሳኔዎችን በዳቮስ እንደሚወያዩበት ይጠበቃል፡፡