ባለፉት 25 አመታት የተከሰቱት ከባድ የርዕደ መሬት አደጋዎች የትኞቹ ናቸው?
ታህሳስ 26፣2004 በበርካታ ሀገራት መጠኑ በሬክተር ስኬል 9.1 የሆነ ርዕደ መሬት ባስከተለው ሱናሚ 230ሺ ሰዎች ሞተዋል
አርብ አመሻሽ ላይ በሞሮኮ የተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ ከ2ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸው እንዲያል ምክንያት ሆኗል
አርብ አመሻሽ ላይ በሞሮኮ የተከሰተው የርዕደ መሬት አደጋ ከ2ሺ በላይ ሰዎች ህይወታቸው እንዲያል ምክንያት ሆኗል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል።
ባለፉት 25 አመታት የተከሰቱትን የርዕደ መሬት አደጋዎች ኤፒ እንደሚከተለው ዘርዝሯቸዋል።
(የጊዜ አቆጣጠሩ እንደፈረንጆቹ ነው።)
-መስከረም 8፣ 2023 በሞሮኮ የተከሰተው መጠኑ በሬክተር ስኬል 6.8 ሲሆን ከ2ሺ ሰዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጓል
-በየካቲት6፣2023 በቱርክ እና ሶሪያ የተከሰተው ርዕደ መሬት መጠኑ በሬክተር ስኬል 7.8 ሲሆን ከ50ሺ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል
-ሚያዝያ 25፣2015 በኔፖል መጠኑ በሬክተር ስኬል 7.8 በሆነ የርዕደ መሬት አደጋ 8ሺ 800 ሰዎች ሞተዋል
-መጋቢት 11፣2011 በጃፖን ሰሜን ምስራቅ ጫፍ የተከሰተው መጠኑ በሬክተር ስኬል 9.0 የሆነው የርዕደመሬት አደጋ የ18ሺ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል
-ጥር 12፣2010 በሀይቲ የተከሰተው ርዕደ መሬት በሬክተርስኬል 7.0 ሲሆን ከ100ሺ በላይ የሆኑ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል
-ግንቦት 12፣2008 በቻይና የተከሰተው በሬክተር ስኬል 7.9 የሆነው ርዕደ መሬት ከ87ሺ በላይ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል
-ግንቦት27፣2006 በኢንዶኔዝያ ጃቫ ደሴት ላይ በተከሰተው መጠኑ በሬክተር ስኬል 6.3 በሆነው የርዕደ መሬት አደጋ 5ሺ 700 ሰዎች ሞተዋል
-ጥቅምት 8፣2005 በፖኪስታን ካሽሚር ግዛት መጠኑ በሬክተር ስኬል 7.6 በሆነ ርዕደ መሬት 80ሺ ሰዎች ሞተዋል
-ታህሳስ 26፣2004 በበርካታ ሀገራት መጠኑ በሬክተር ስኬል 9.1 የሆነ ርዕደ መሬት ባስከተለው ሱናሚ 230ሺ ሰዎች ሞተዋል
-ታህሳስ 26፣2003 በኢራን መጠኑ በሬክተር ስኬል 6.6 የሆነ ርዕደ መሬት 20ሺ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል
-በጥር 26፣2001 በህንድ መጠኑ በሬክተር ስኬል 7.6 በሆነ ርዕደ መሬት 20ሺ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል