ለፍንዳታው እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለም ተነግሯል
የሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ፍንዳታ ከፍተኛ የፍንዳታ አደጋ መድረሱ ተነገረ።
በሞቃዲሾ ከተማ ሌሊት ላይ በደረሰው ፍንዳታ ቢያንስ የ5 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ 23 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውም ተነግሯል።
ፍንዳታውን ተከትሎም የሞቃዲሾ ነዋሪወች በድንጋጤ ከእንቅልፋቸው ነቅተዋልም ነው የተባለው።
ሮይተርስ እማኙን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ፍንዳታው ከደረሰበት ቦታ ላይ የጭስ ይታይ ነበር እንደሁም የጥይት ድምጽ ሲሰማ ነበር ብሏል።
ለጥቃቱ እስካሁን ኃለፊነት የወሰደ አካል ባይኖርም፤ አልሻባባ በተለያዩ ጊዜያት ከመፈጽማቸው ጥቃቶች ጋር በተያያዘ አልሻባብ ሊሆን እንደሚችል ይገማታል።
ሰኞ እለት የሶማሊያ የጸጥታ ኃይሎች በደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍል የታችኛው ሸበሌ ጠቅላይ ግዛት አፍጎዬ አከባቢ በአሸባሪው የአልሸባብ እንቅስቃሴ ላይ ልዩ ዘመቻ መፈጸሙ የሚታወስ ነው።
በዘመቻው የኦፊሴላዊው የሰራዊት ድምጽ ራዲዮ የስለላ አገልግሎቱ፤ ሶስት የአልሸባብ ንቅናቄ አመራሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ማስታወቁም ጭምር ይታወቃል።
በቅርቡ የሶማሊያ መረጃና ደህንነት ክፍል፤ የአልሸባብን ጥቃት ቀድሞ ለመከላከል የሚያችሉ እንደ ፈንጂዎችን መያዝ፣ ጥቃትን ማክሸፍ እና ከመሪዎች እና የተለያዩ አካላት መካከል የአሸባሪ ድርጅት አባላትን በቁጥጥር ስር ማዋልን የመሳሰሉ ዘመቻወችን አጠናክሮ ቀጥሎበታል።