በሶማሊያ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ እየተነገረ ነው
ጥቃቱ የተፈፀመው “በጀነራል ዓብዱልከሪም ዮሱፍ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከል” ነው ተብለዋል
ጥቃቱ የሶማሊያው ኢታዦር ሹም ኦዶዋ ዮሱፍ በእልሻባብ ላይ ተከታታይ ኦፕሬሽኖች እናደርጋለን ማለታቸው ተከትሎ ነው
በሶማሊያ በአጥፍቶ ጠፊ በጸፈተመ የቦምብ ጥቃት በርካታ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡
በሶማሊያ በአጥፎ ጠፊ በሞቃዲሾ አቅራብያ በሚገኘው ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከል በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ሺንዋ ዘግቧል፡፡
በጀነራል ዓብዱልከሪም ዮሱፍ ስም በተሰየመው ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእክል በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች እንደነበሩም ነው እየተገለጸ ያለው፡፡ በተፈፀመ የአጥፍቶ ማጥፈት ጥቃት በርካቶች ሳይጎዱ እንዳልቀሩም ጭምር፡፡
ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከሉ አሁን ላይ በሀገሪቱ ፖሊስ መኮንኖች ስር እንደሚገኝ እንዲሁም ከጥቃቱ የተረፉትን ህይወት የማዳን ስራ እየተከናወነ እንደሆነም ተግለፀዋል፡፡
ዝነኛው ጀነራል ዓብዱልከሪም ዮሱፍ እ.ኤ.አ በሞቃዲሾ ከተማ በሚገኘው ሳሃፊ ሆቴል ውስጥ ሳሉ በአልሻባብ መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡
አልሻባብን ለማጥፋት ሲደረግ በነበርው ጥረት የነበራቸው ከፍተኛ ድርሻ ለማስታወስ በሚል ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማእከሉ በእሳቸው(በጀነራል ዓብዱልከሪም ዮሱፍ)ስም መሰየሙና በጣም ከሚነገርላቸው ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች መሆኑም ጭምር የሚታወቅ ነው፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመው በሶማሊያው ኢታዦር ሹም ኦዶዋ ዮሱፍ ራገህ የሚመራው ሶማሊያ ጦር በእልሻባብ ላይ ተከታታይ ኦፕሬሽኖች አደርጋለው ማለቱን ተከትሎ ነው፡፡
እስካሁንም ባለፉት ሶስት ሳምታት ብቻ ከ200 የሚልቁ ታጣቂዎች መደምሰሳቸው የሀገሪቱ ሚድያ ማረጋገጡን ይ አድርገዋል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አልሻባብ ለመደምሰስ የሚደረገውን ትግል ለማጎልበት በመቶዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ኬንያ እንደሚያሰማሩ መግለጻቸው የአሜሪካ መከላኬ ሚኒሰቴር ባለፈው ሳምንት መግለፁም እንዲሁ የሚታወስ ነው፡፡