የሃገሪቱ መንግስት በዛሬው ዕለት በተወሰደ እርምጃ ሶስት የሽብር ቡድኑ አባላትን ገድያለሁ ብሏል
ሶማሊያ በጽንፈኛው አልሻባብ ላይ እርምጃ መውሰዷን ቀጥላለች።
የሶማሊያ ልዩ ሀይል ከጁባላንድ የደህንነት ሀይል ጋር በወሰደው እርምጃ ሶስት የአልሻባብ ታጣቂዎችን መግደሉን ገልጿል።
ወታደራዊ ዘመቻው የተካሄደው በደቡባዊ ሶማሊያ ስር ባለችው የታችኛው ጁባ ክልል እንደሆነ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
አልሻባብ በሶማሊያ እስላመዊ መንግስት እመሰርታለሁ በሚል የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ሲሆን በሌሎች አገራት ከሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች ጋርም በጋራ እንደሚሰራ የሽብር ቡድኑ ከዚህ በፊት ባወጣቸው መግለጫዎች አስታውቋል።
ሶማሊያ ከ30 ዓመታት በኋላ ሲኒማ ማሳየት ጀመረች
በዚህም ምክንያት የሶማሊያ መንግስት ከአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ጦር ወይም አሚሶም ጋር በመቀነባጀት በዚህ የሽብር ቡድኑ ላይ ተደጋጋሚ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል።
የሶማሊያ ጦር ከአንድ ወር በፊት የአልሻባብ ጦር ምክትል አዛዥን መግደሉ ይታወሳል።
አልሻባብ ከ10 ዓመት በፊት የሶማሊያ ከተሞችን የተቆጣጠረ ሲሆን አሁን ላይ በተወሰደበት የተቀናጀ ወታደራዊ እርምጃ ተዳክሞ በገጠር ቀበሌዎች ውስጥ እንደሚንቀሳቀስ ዘገባው አክሏል።