በሶማሊያ በፕሬዝዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ በተጠመደ ቦንብ ሰባት ሰዎች ተገደሉ ተባለ
ከሞቱ ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች ስምንት ሰዎች በጥቃቱ ቆስለዋል
ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም ተብሏል
በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሹ ቅዳሜ ዕለት በፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ በሚገኝ መስቀለኛ መንገድ ላይ በአንድ የአጥፍቶ ጠፊ የመኪና ፍንዳታ ቢያንስ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን አንድ ባለሥልጣን አስታወቁ።
- ሶማሊያ ከ30 ዓመታት በኋላ ሲኒማ ማሳየት ጀመረች
- የሶማሊያ ጦር ኃይል 50 የአልሸባብ ታጣቂዎችን መግደሉን አስታወቀ
- የሶማሊያ ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር በብሔራዊ ደህንነት ሹመት ዙሪያ ወደ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል
በሞቃዲሾ የካምጃጃብ ዲስትሪክት ሃላፊ ሙአይዬ ሙደይ ለሮይተርስ እንደገለፁት በኤልጋአብ መስቀለኛ መንገድ ላይ በተጠመደ የአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ሰባት ሰዎች ሲሞቱ ስምንት ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል፡፡
ለጥቃቱ ተጠያቂው ማን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም ፣ ነገር ግን መንግስትን ለመገልበጥ እና የእስልምና ሕግ ትርጓሜውን ለመጫን የሚፈልገው አልሸባብ በተደጋጋሚ እንደዚህ ዓይነት ፍንዳታዎችን እንደሚያካሂድ ዘገባው ጠቅሷል፡፡
በፍንዳታው ቦታ ላይ የአይን እማኝ ለየሮይተርስ እንደገለጸው በፍንዳታው ሰባት መኪኖች እና ሦስት አነስተኛ ተሽከርካሪዎችና ወድመዋል ፣ መስቀለኛ መንገዱም በሙሉ በደም ተሸፍኗል።