ሃገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት እንዲመሩ የተመረጡት ደ ክሩ ነገ ሃሙስ ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ ተብሏል
ያለመንግስት በቆየችው ቤልጂዬም መንግስት ለመመስረት ስምምነት ላይ ተደረሰ
ያለፉትን 5 ወራት ያለ መንግስት ባሳለፈችው ቤልጂዬም የፌዴራል መንግስት ለመመስረት ስምምነት ላይ ተደረሰ፡፡
ከወርሃ ግንቦቱ ምርጫ ወዲህ ለመስማማት ባለመቻላቸው አንድ ጥምር የፌዴራል መንግስትን ለመመስረት ተስኗቸው የነበሩት ሰባት ተፎካካሪ ፓርቲዎች አሁን ተጣምረው መንግስት ሊመሰርቱ ከሚችሉበት ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በስምምነቱ መሰረትም ሊበራሉ የፍሌሚሽል ክልል ተወካይ አሌክሳንደር ደ ክሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሃገሪቱን እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡
የ44 ዓመቱ ደ ክሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት የሃገሪቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ነበሩ፡፡
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ነገ ቃለ መሃላ የሚፈጽሙ ሲሆን የጥምር መንግስቱ አባል የሆኑ ፓርቲዎች ዛሬ የተናጠል ስብሰባ አድርገው የካቢኔ ተወካይዎቻቸውን እንደሚመርጡ ይጠበቃል እንደ ብራሰልስ ታይምስ ዘገባ፡፡
የቋንቋ ልዩነቶች ፖለቲካውን በሚያሾሩባት ቤልጂዬም ያለ መንግስት ወራትን ካለ መንግስት ማሳለፍ አዲስ አይደለም፡፡ ከአሁን ቀደምም እንዲህ ዓይነቱ ለ541 ያህል ቀናት አጋጥሟል፡፡
ቤልጂዬም ፍሌሚሽ፣ ውለን፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን እና የብራሰልስ ማህበረሰብ በሚሉ ክልላዊ አደረጃጀቶች የተዋቀረች መሆኗ የሚታወስ ነው፡፡