በፖኪስታን በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከአንድ ሺ አለፈ
ቻይና ለፖኪስታን ድጋፍ በማድረግ ላይ ነች
ከፓኪስታን ሰሜናዊ አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ በትዕዛዝ መፈናቀላቸውን መንግስት ገልጿል
በፓኪስታን ከሰኔ ወር ጀምሮ በጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 1ሺ33 መድረሱን የሀገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ መከላከል ባለስልጣን ባወጣው አሃዛዊ መረጃ ያሳያል።
ከሰኔ ወር ጀምሮ የጣለው ከባድ ዝናብ ከ33 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በማጥቃቱ በሀገሪቱ ባለፉት 24 ሰዓታት 119 ሰዎች መሞታቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
ከፓኪስታን ሰሜናዊ አካባቢዎች በሺዎች የሚቆጠሩ በትዕዛዝ መፈናቀላቸውን መንግስት ገልጿል።
በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ ክልል ውስጥ የምትገኝ የሲንዲ ግዛት አንድ ባለስልጣን የጎርፍ መጥለቅለቁ ከፈረንጆቹ በ2010 ከነበረው የከፋ መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህም በፓኪስታን ታሪክ ውስጥ እጅግ የከፋ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተደርጎ ይቆጠር ነበር።
በፈረንጆቹ በ2010 በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 1,700 በፓኪስታን ገድለዋል ፣ አብዛኛዎቹ የሲንዲ ግዛት ነዋሪዎች ናቸው።
ባለፈው ረብኡ ቻይና 25,000 ድንኳኖችን እና የእርዳታ ቁሳቁሶችን ጨምሮ የአስቸኳይ ጊዜ ሰብአዊ ዕርዳታ ወዲያውኑ ልካለቸ።