ሱዳን 84 ዜጎቿን በጎርፍ አደጋ ማጣቷን ገለጸች
የጎርፍ አደጋው ከሰው ህይወት ባለፈ ከ27 ሺህ በላይ ቤቶችን አውድሟል
የጎርፍ አደጋው የደረሰው በ11 የሱዳን ግዛቶች ሲሆን ከ65 ሺህ በላይ ዜጎችን አፈናቅሏል ተብሏል
ሱዳን 84 ዜጎቿን በጎርፍ አደጋ ማጣቷን ገለጸች።
ሱዳን በያዝነው የክረምት ወቅት በተከሰተ የጎረፍ አደጋ በትንሹ 84 ዜጎቿን እንዳጣች የሀገሪቱ መንገስት አስታውቋል።
- ከህዳሴ ግድቡ ጋር ተያይዞ በዘንድሮው ክረምት “የደረሰብኝ የጎርፍ አደጋ የለም”- ሱዳን
- በሱዳን በጣለ ከባድ ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቀለቁ
የሀገሪቱ ብሔራዊ የሲቪል ዜጎች ጥበቃ ምክር ቤት ቃል አቀባይ እንዳሉት የጎረፍ አደጋው ከሞት ባለፈ 67 ሰዎችን አካል እንዳጎደለ ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
አደጋው የደረሰው በአገሪቱ 11 ግዛቶች ሲሆን ከ27 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን እንዳወደመ ተገልጿል።
በሱዳን በየዓመቱ የጎረፍ አደጋ የተለመደ ሲሆን ዜጎችን ከመግደሉ ባለፈ ለንብረት ውድመት እንደሚዳርግ የተገለጸ ሲሆን የዘንድሮው የጎረፍ አደጋ አስከ ቀጣዩ ጠቅምት ድረስ ሊዘልቅ ይችላል ተብሏል።
እስካሁን ባለው የክረምት ወቅት በደቡባዊ ሱዳን ክፍል 50 መንደሮች ክፉኛ በጎርፍ ተጠቅተው ከ65 ሺህ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸውን የተመድ ሪፖርት ያስረዳል።
ባሳለፍነው ዓመት በተመሳሳይ የክረምት ወራት በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ሱዳን የሶስት ወራት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንድታውጅ ያስገደዳት ሲሆን ከ110 ሺህ በላይ ቤቶች በጎርፍ ወድመው ከ650 ሺህ በላይ ዜጎች መጎዳታቸው ይታወሳል።