ሱዳን በከባድ ዝናብና ጎርፍ መቸገሯ ተገልጿል
ጥቂት የማይባሉ የሱዳን አካባቢዎች በከባድ ዝናብና ጎርፍ መቸገራቸው ተገለፀ።
በዚህ ሳምንት ብቻ ብሉ ናይል ተብሎ በሚጠራው የሃገሪቱ አካባቢ ብቻ 77 ሱዳናውያን በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
በአደጋው 9 ሺ ገደማ ቤቶች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውና 27 ሺ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ሲጂቲኤን ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በአደጋው ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች የህዝብ መገልገያ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል።
የአደጋው ሰለባዎችም መኖሪያቸውን አጥተው በጊዜያዊነት በድንኳን ውስጥ ለመጠለል እና እርዳታ ለመጠባበቅ ተገደዋል።
ከአንዳንድ በጎ ፈቃደኞች እና የአካባቢው የበጎ አድራጎት ተቋማት ከሚያገኙት ድጋፍ በስተቀር የሃገራቸው መንግስት እየደገፋቸው እንዳይደለም ነው የገለፁት።
ሶስተኛ ዙር ሙሌቱ ከሰሞኑ የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሱዳን ሊያጋጥሙ የሚችሉ መሠል የጎርፍ አደጋዎችን የማስቀረት ጥቅም እንዳለው በሱዳናውያን ጭምር ይነገራል።