በአሜሪካ የሚገኘው ይህ ስፍራ የጎብኚዎችን ቀልብ የሳበ ስፍራ ተብሏል
በዓለም ሞቃታማው ስፍራ የሞት ሸለቆ
በፈረንጆቹ በ1849 ላይ አውሮፓዊያን ወርቅ ለማውጣት አሁን ላይ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ እንደሄዱ ይነገራል፡፡
እነዚህ ወርቅ አውጪዎች በዚህ ሞቃታማ የሸለቆ ስፍራ ካቀኑ በኋላ ስፍራው እንዳሰቡት ወርቅ የሚገኝበት ሳይሆን ለህይወት አስቸጋሪ ቦታ መሆኑን ይረዳሉ፡፡
ለወርቅ ማውጣት ወደ ስፍራው ካቀኑ ሰዎች መካከልም አንዱ ወደ ሸለቆው ገብቶ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ የሞት ሸለቆ የሚል ስያሜን አግኝቷል፡፡
ይህ የሞት ሸለቆ ባሳለፍነው ዓመት ሀምሌ ወር ላይ 54 ነጥብ 4 በመቶ ድግሪ ሴልሺየስ ሙቀት በማስመዝገብ በዓለም ሞቃታማ በመሬት ላይ ያለ ስፍራ ለመባል በቅቷል፡፡
ከባህር ወለል በላይ የመሬት 86 ሜትር ርቀት ያለው ይህ ስፍራ ሞቃታማ በሆኑ በተራራዎች የተከበበ ሲሆን ምንም አይነት ርጠርበታማ እና እጅግ አነስተኛ ዓመታዊ ዝናብ የሚዘንብበት ስፍራም እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በዚህ ሞቃታማ ስፍራ ከአንድ ሺህ በላይ የእጸዋት፣ 51 አጥቢ እንስሳት፣ 36 ተሳቢዎች እና 307 የአእዋፍ ብዝሃ ህይወት የኖሩበታልም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ተመራማሪዎች በዚህ ስፍራ ከፍተኛ ሙቀትን ተቋቁመው መቆየት የሚችሉ ዝርያዎችን በማላመድ ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን ስፍራው የጎብኚዎችን ቀልብ እንደሳበ ተገልጿል፡፡