በሩሲያ ለማረፍ 5ኪ.ሜ አካባቢ ሲቀረው ከበረራ መቆጣጣሪያ ራዳር ውጭ የሆነው አውሮፕላን ስብርባሪ ተገኘ
በሩሲያ ሩቅ ምስራቅ ካምቻትካ ግዛት ለማረፍ 5 ኪሎሜትሮች አካባቢ ሲቀሩት ከበረራ መቆጣጠሪያ ውጭ ሆኖ የጠፋው አውሮፕላን ስብርባሪ መገኘቱን ባለስልጣናትን መናገራቸውን ኤፒ ዘግቧል፡፡
22 መንገደኞችንና 6 የበረራ አስተናጋጆችን አሳፍሮ የነበረው አንቶኖቨ ኤኤን-26 የተባለው አውሮፕላን ከፔትሮፓቭሎቭስክ ከተማ ወደ ኦክሆስትክ ባህር ዳርቻ ወደምትገኘው ካምቻስኪ ከተማ በሚበርበት ወቅት፤ከበረራ መቆጣጠሪያው ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋረጠ፤ከበራራ መቆጣጠሪያ ራዳር ውጭም ሆኗል፡፡
አውሮፕላኑ ከበረራ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ውጭ የሆነው ለማረፍ ሲቃረብ ነበር፡፡የካምቻትካ አስተዳዳሪ ቪላድሚር ሶሎዶቭ እንደተናገሩት የአውሮፕላኑ ዋና ክፍል በባህሩ ዳርቻ መሬት ላይ መገኘቱንና ሌሎች ስብርባሪዎች ደግሞ በኦክሆስትክ ባህር ዳርቻ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
እንደ ሩሲያ መገናኛ ብዙህሃን ዘገባ በአውሮፕላኑ ላይ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች በህይወት አልተረፉም ተብሏል፡፡ አውሮፕላኑ በባለቤትንት ያስመዘገበው ካምቻትካ አቬሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሆን አውሮፕላኑ ከፈረንጆቹ 1982 ጀምሮ ስራ ላይ ነበር ተብሏል፡፡
የኩባንያው ዳሬክተር አሌክሶ ካባሮፕ አውሮፕላኑ ከመብረሩ በፊት የቴክኒክ ችግር አልነበረበትም ብለዋል፡፡ የሩሲያ ባለስልጣናት አውፕላኑ ለመከስከስ ያበቃው ምክንያት ምን እንደሆነ ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡ አውሮፕላኑ ሊያርፍ ጥቂት ኪሎሜትሮች ሲቀሩ ነበር ከበረራ ግንኙነት ውጭ ሆኖ ሊከሰከስ የቻለው፡፡
ሩሲያ በአንድ ወቅት በአውሮፕላን አደጋዎች መጥፎ ስም የነበራት ሲሆን የአየር ትራፊክ ደህንነቷን ለማሻሻል በሰራችው ስራ ችግሩን መቀየሯ ቢገልጽም አሁን የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ገጥሟታል፡፡