ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ልጃቸው ሼክ ካሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድን አልጋ ወራሽ አድርገው ሾሙ
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ 5 ታሪካዊ የተባሉ ውሳኔዎችና አዋጆችን አሳልፈዋል
ከተላለፉ ውሳኔዎች መካከልም የምክትል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ አዳዲስ ሹመቶች ይገኙበታል
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አምስት ታሪካዊ የተባሉ ውሳኔዎችና አዋጆችን መሳለፋቸው ተገለፀ።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ካሳለፏቸው 5 ታሪካዊ ውሳኔዎች እና አዋጆች መካከልም አዳዲስ የአመራር ሹመቶች እንደሚገኙበት ታውቋል።
ፕሬዝዳንቱ በትናትናው እለት ባሳለፉት ውሳኔ መሰረትም የአረብ ኢሚሬትስ የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ወንድማቸው ሼክ መንሱር ቢን ዛይድ አል ናህንያን የሀገሪቱ ምክትል ፐሬዝዳንት በማድረግ ሾመዋል።
- የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ 2023ን "የዘላቂነት ዓመት" በሚል አወጁ
- ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አረብ ኤሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና ተቀጥላች አሉ
በዚህም መሰረት ሼክ መንሱር ቢን ዛይድ አል ናህንያን፤ የአረብ ኢሚሬት ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዱባይ ገዢ ከሆኑት ሼክ መሃመድ ቢን ረሺድ አል መክቱም ጎን ለጎን በምክትል ፐሬዝዳንትነት ያገልግላሉ።
በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን የመጀመሪያ ልጃቸው የሆነውን ሼክ ካሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድን የአቡዳቢ ልዑል አልጋ ወራሽ አድርገው መሾማቸውም ታውቋል።
እንዲሁም ሼክ ሀምዛ ቢን ዛይድ አል ናህንያን እና ሼክ ታህኖም ቢን ዛይድ አል ናህንያን ደግሞ የአቡዳ ምክትል ገዢዎች ተደርገው መሾማቸውም ተመላክቷል።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በተጨማሪም የአቡዳቢ ኢሚሬትስ የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት እንደገና ለማቋቋም አዋጅ ማስተላለፋቸውም ነው የተነገረው።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ነበር የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት በመሆን የተሸሙት።
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አንደኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸው በተቃረበበት ወቅት ያሳለፏቸው ውሳኔዎች ሀገሪቱን በተሸለ መልኩ ወደ ፊት ለማራመድ ይረዳሉ ተብሎ እምነት እንደተጣለባቸውም ተነግሯል።