ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አረብ ኤሚሬትስ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና ተቀጥላች አሉ
የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማትና ደህንነት ጉባዔ በሳዑዲ አረቢያ ተካሄደ
የኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ለ1443 የሂጅራ ስኬት ለሳውዲ ንጉስ የደስታ መልእት አስተላልፈዋል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ሀገራቸው በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና መረጋጋት ላይ ዋነኛ አጋር ሆና እንደምተጥል አረጋገጡ።
የገልፍ ሀገራት-አሜሪካ የልማትና ደህንነት ጉባዔ በዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ ጄዳህ ተካሂዷል።
በጉባዔው ላይ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን እና የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሃመድ ቢን ዛይድን ጨምሮ ሌሎችም የገልፍ ሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት፤ ሀገራቸው በቀጠናው ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማሳደግ እንዲሁም አለም አቀፋዊ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን እና የጋራ ችግሮችን ለመጋፈጥ ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠዋል።
አረብ ኢሚሬትስ በአለም አቀፍ ግንኙነት ላይ የምትከተለው ፖሊሲ በሚዛናዊነት ላይ የተመሰረተ እና ከአለም ሀገራት ጋር የጋራ የጥቅም መሰረትን በማስፋት ለሀገራዊ ልማትና ሰላምና መረጋጋት ግቦችን ማስፈን መሆኑን አስረድተዋል።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ እንዳሉት "በቀጠናችንም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ትልቅነት ለማንም የተሰወረ አይደለም” ያሉ ሲሆን፤ “እንዚህን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እና የህዝቦቻችንን ምኞት ለማሳካት የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር ይጠይቃል” ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ፕሬዝዳንት አክለውም ለ1443 የሂጅራ ስኬት ለሳዑዲ አረቢያው ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱላዚዝ አል ሳኡድ የደስታ መልእክት አስተላልፈዋል።
ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የሳዑዲ ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማን፤ “ይህ የመሪዎች ጉባኤ ሀገሮቻችንን ከአሜሪካ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።
“ዘላቂ ልማትን ለማምጣት የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ያገናዘበ ሚዛናዊ አካሄድ መከተልን ይጠይቃል” ያሉት መሃመድ ቢን ሰልማን፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተግዳሮቶች ለመቋቋም የካርበን ልቀተን መቀነስ ልቀትን መሰረት ያደረገ አሰራር መከተላቸውን አስታውቀዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳነት ጆ ባይደንም በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ለመሰረተ ልማት እና ለንጹህ የኃይል ልማት በቢሊየን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ኢንቨስት እናደርጋለን ብለዋል።
የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በበኩላቸው፤ ቀጠናው እና ሀገሮቻችን አሁን ዓለማችንን እያጋጠመ ላለው ችግር መፍትሄ ማፈላግ ላይ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።