ሞሃመድ ቢን ዛይድ "ከአሜሪካ ጋር ጋር ያለን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ጠንካራ ነው" አሉ
ፕሬዝዳንቱ "በሁለቱ ሀገራት መካከል ዘላቂ ልማት የሚደግፉ መርሃ-ግብሮች መጀመራቸውን በደስታ እንቀበላለን" ብለዋል
አረብ ኢምሬት እና አሜሪካ የ100 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ተፈራርመዋል
ሞሃመድ ቢን ዛይድ "ከአሜሪካ ጋር ጋር ያለን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ጠንካራ ነው" አሉ።
የአረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ሀገራቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ፕሬዚዳንታዊ አስተባባሪ አሞስ ሆችስቴይን ጋር ተገናኝተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በዚህ ስትራቴጂካዊ ግንኙነት ለሁለቱ ወዳጅ አገራት እና ለዓለም የተሻለ መፃኢ እድል ለመፍጠር ፍላጎት እንዳለ አመልክተዋል።
"በሁለቱ አገራት መካከል ዘላቂ ልማት የሚደግፉ መርሃ-ግብሮች መጀመራቸውን በደስታ እንቀበላለን" ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ሼል መሃመድ ቢን ዛይድ ይህን ያሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና ዩናይትድ ስቴትስ የ100 ቢሊዮን ዶላር ስልታዊ የተባለ የአጋርነት ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ ነው።
ስምምነቱ እ.አ.አ በ2035 በሁለቱ አገራትና በሌሎችም 100 ጊጋዋት ንጹህ ኃይል የማምረት የሚያስችል ነው።
እንደ ኢሚሬትስ የዜና ወኪል ዘገባ ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ከአቡዳቢ አለም አቀፍ የነዳጅ አውደ ርዕይ እና ጉባኤ ጎን ለጎን ከዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ፕሬዚዳንታዊ አስተባባሪ አሞስ ሆችስቴይን ጋር ተገናኝተዋል።
በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና አሜሪካ መካከል ያለለውን ስትራቴጂያዊ ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።