የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ተወያዩ
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በሩሲያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ነው
ፕሬዝዳንት ፑቲን “አረብ ኢሚሬትስ በገልፍ ቀጠና ትልቅና ተደማጭነት ሚና ያላት ሀገር ናት” ብለዋል
የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን ከሩሲያው አቻው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በሩሲያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው እለት ሞስኮ መግባታቸውን የኢሚሬትስ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን በጉብኝት ላይ ለሚገኙት የአረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በቅዱስ ፒተርበርግ በሚገኝ ቤተ መንግስት አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ እና ፕሬዝዳንት ፑቲን በአረብ ኢሚሬትስ እና ሩሲያ ሁለትዮሽ ግንኙነቶች ዙሪያ እንዲሁም በቀጠናዊ እና በዓለምአቀፋዊ ሁነቶችን አንስተው መወያየታቸው ታውቋል።
የሩሲያው ፕሬዝዳት ቭላድሚር ፑቲን በውይይቱ ወቅት፤ በገልፍ ቀጠና ከፍተኛ ሚና ከምትጫወተው አአረብ ኤምሬትስ ጋር ቀጠናዊ ጉዳዮችን እና ችግሮችን አንስቶ መወያየት ወሳኝ አንደሆነ አስታውቀዋል።
በሶሪያ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ያስታወቁት ፐሬዝዳንት ፑቲን፤ ፕሬዳንት መሃመድ ቢን ዛይድ ጊዜ ሰጥተው ለጉብኝት ወደ ሞስኮ በመምጣታቸውም አመስግነዋል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን አክለውም፤ የአረብ ኤምሬትስ እና የሩሲያ ግንኙነት ስኬታማ የሆነ እድገት እያሰመዘገበ ለሰመሆኑ ምስክርነት ሰጥተዋል።
ፕሬዝዳት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በበኩላቸው አረብ ኤምሬትስ በአለም ላይ የሰላም እና መረጋጋት መሰረትን ለማጠናከር የበኩሏን ጥረት እንድታደርግ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ እየታዩ ላሉ ቀውሶች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት ሀገራው እንደመትሰራም ፕሬዝዳነቱ አረጋግጠዋል።
ሩሲያ፤ አረብ ኤሚሬትስ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ላንጸባረቀቸው ሚዛናው አቋም እንደምታመሰግን የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከወራት በፊት በሞስኮ ጉብኝት ላደረጉት የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡
ሀለቱም ሀገራት በተለያዩ መስኮች ዘርፈ ብዙ ትብብር እንደሚያደርጉ ይተወቃል፡፡
በተለይም የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከዓረቡ ዓለም ያደገች ሀገር እንደመሆኗ ሞስኮ-አቡዳቢ ጋር የምታደርገው ትብብር የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በሀገራቱ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ደርሷል።