የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ 2023ን "የዘላቂነት ዓመት" በሚል አወጁ
ዓላማውም አረብ ኤምሬትስ የዘላቂነት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍና በኃይል፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎችም ዘርፎች አዳዲስ መፍትሄዎችን በመፈለግ ሚናዋን ለማጉላት ነው
የ"የዘላቂነት ዓመት" ውጥኖች የሚቆጣጠሩት ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ማንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያንና ሼክ ማርያም ቢንት መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እንደሆኑ ተነግሯል
አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን “ዛሬ ለነገ” በሚል መሪ ቃል የፈረንጆች 2023 ዓመት "የዘላቂነት ዓመት" ሲሉ አውጀዋል።
ይህም ሀገሪቱ ከምታስተናግደው 28ኛው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 28) ጋር መሳ ለመሳ የሚሄድ ነው።
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት "2023 በአረብ ኤምሬትስ የዘላቂ ዓመት ይሆናል፤ ከኮፕ 28 አስተናጋጅነታችን ጋር ይገጣጠማል" ብለዋል።
ታሪካችን እና አካሄዳችን አካባቢን እና የሀብት ዘላቂነትን መጠበቅ የማያቋርጥ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ "እናም ህብረተሰባችን የሀገራችንን የሰለጠነ ገጽታ ያካተቱ አዳዲስ ሀሳቦችን እና ጥራት ያላቸውን ጅምሮች እንዲወስድ እጋብዛለሁ" ብለዋል።
“ዛሬ ለነገ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው "የዘላቂነት ዓመት" በተለያዩ ተነሳሽነቶቹ፣ ዝግጅቶች እና ተግባራት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በዘላቂነት ልምድ ላይ ብርሃንን ለማብራት ያለመ ነውም ተብሏል።
በተጨማሪም በዓመቱ ስለ አካባቢ ዘላቂነት ጉዳዮች ግንዛቤን ማሳደግ፣ ዘላቂ ልማትን በማሳካት የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማበረታታት እና በዚህ መስክ የበለጠ የበለፀገ ወደፊትን ለመገንባት ሀገራዊ ስልቶችን እንደሚደገፉ ተጠቁሟል።
ዓላማው አረብ ኤምሬትስ የዘላቂነት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተለይም በኃይል፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎችም ዘርፎች ሁሉንም የሚጠቅሙ አዳዲስ መፍትሄዎችን በመፈለግ ረገድ የምትጫወተውን ሚና ለማጉላት ነው ተብሏል።
የ"የዘላቂነት ዓመት" ውጥኖች የሚቆጣጠሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ማንሱር ቢን ዛይድ አል ናህያን እና ሼክ ማርያም ቢንት መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እንደሆኑ ተነግሯል።
ፕሬዝዳንቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከተመሰረተችበት ጊዜ ጀምሮ አካባቢን በመጠበቅ ረገድ ትልቅ አርአያ መሆን እንደቻለች ተናግረዋል።