
ብልጽግና ፓርቲ አቶ ተመስገን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል
አቶ ደመቀ መኮንን ከብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳትነት መልቀቃቸውን ፓርቲው አስታወቀ።
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ የፓርቲውን የአመራር የመተካካት መርህንና የአሰራር ስርዓት በመከተል ዛሬ ባካሄደው ማጠቃለያ ስብሰባ በሙሉ ድምፅ አቶ ደመቀ መኮንን መሸኘቱን አስታውቋል።
በምትካቸውም የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ የነበሩትን አቶ ተመስጌን ጥሩነህን ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል።