ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ንግግራቸው ምን አሉ?
ኢትዮጵያ አጀንዳ በሚቀረፅላቸውና ቀለብ በሚሰፈርላቸው ሚዲያዎች ተከሳ፣ መርህ አልባ በሆነ ፖለቲካ ተፈርዶባታል ብለዋል
በግድቡ ዙሪያ በአፍሪካ ሕብረት መሪነት በሚካሄደው ድርድር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት ላይ ለመድረስ ተስፋ እናደርጋለን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኒውዮርክ እየተካሄ ባለው በ76ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።
አቶ ደመቀ በንግግራቸው ኢትዮጵያ ከሶስት ዓመት በፊት ተስፋ ሰጪ የለውጥ ጉዞ መጀመሯን እንስተው፤ በዚህም ዴሞክራሲ፣ ሰብዓዊ መብት እና ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እንዲሁም ለተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች ላላቸው ቡድኖች የውይይት እና የአንድነት በር እንዲከፈት መደረጉን እንስተዋል።
ሆኖም ግን የለውጥ ሂደቱ በፈተናዎች ውስጥ እያለፈ መሆኑንም የጠቀሱት አቶ ደመቀ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነትን እንደ መገዛት የሚቆጥሩ ቡድኖች ሥርዓት አልበኝነትን ለመፍጠር የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል።
በእነዚህ ሀይሎች በዜጎች ላይ በርካታ ኢ -ሰብአዊ ጥቃት፣ አመፅ በማነሳሳት እና በንብረት ውድመት ማስከተላቸውን በመጥቀስ፤ በኢትዮጵያ ጦር ላይ ጥቃት እስከ መስነዘር መድረሱንም አስታውሰዋል።
ባለፈው ዓመት ጥቅምት 24 ምሽት ወንጀለኛው ቡድን በተቀነባበረው ዕቅድ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጥቃት እንደሰነዘረበት ያስተወሱት አቶ ደመቀ፤ በዚህም የደንብ ልብስ የለበሱ ወንድና ሴት የሰራዊቱ አባላት ተገድለዋል ብለዋል።
ይህንን ተከትሎም መንግስት ህግን ለማስከበር እና ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ እርምጃ መውሰዱንም ተናግረዋል።
መንግስት የሰብአዊ ድጋፍ ሲያደረግ ቡድኑ ድጋፉ እንዲደናቀፍ እና የዜጎች ስቃይ እንዲበረታ ማድረጉንም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተናሩት።
በውሸት ፕሮፖጋንዳ የተካነው ቡድን በርካታ አፍራሽ ተግባራትን ፈጽሟል ያሉ ሲሆን፤ የውሸት ክስተቶችን አስተጋብቷል፤ቀድሞ በተዘጋጅ ስም የመጣፋት ዝንባሌ ከፍተኛ ዘመቻ አድርጓል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብዓዊ ዕርዳታ የመስጠት ግዴታውን መወጣቱ፣ የተናጠል ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ማወጁ፣ የምርመራ ሥራዎችን እና ተጠያቂነት የማስፈን እርምጃዎችን መውሰዱ የሐሰት ውንጀላዎችን መቀልበስ አልተቻለም።
በዚህ ሰዓት አጀንዳ በሚቀረፅላቸው እና ቀለብ በሚሰፈርላቸው ሚዲያዎች ተከሰን፣ መርህ አልባ በሆነ ፖለቲካ ተፈርዶብን እንዲሁም በተናጠል የተጣለ ማዕቀብ ተደቅኖብን እንገኛለን ብለዋል።
“በቀደሙት ጊዜያት ማእቀቦች በሌሎች ላይ ሲፈፀም መቃወማችን የሚታወስ ሲሆን በተመሳሳይ በኢትዮጵያም ላይ የሚደረግ ፍትህ እና ርቱዕ የሚጎድለው አካሄድ ተግባራዊ እንዳይሆን እንመክራለን፤ ምክንያቱም ጫና የሚያሳድሩ ማንኛውም እርምጃዎች ግንኙነቶችን አሻሽለው አያውቁም”ሲሉም ተናረዋል።
በየትኛውም መልኩ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ የሚገባን ሀይል ኢትዮጵያ እንደማትታገስም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል።
መንግስት የሚወስዳቸውን ጥንቃቄ የተሞላባቸው እርምጃዎች ኢትዮጵያን ከገጠማት የህልውና ፈተና ጋር ተመጣጣኝ ነው ያሉት አቶ ደመቀ፤ ምንም እንኳን አላስፈላጊ ጫናዎች ቢኖሩም፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና የፖለቲካ ነፃነት የማስጠበቅን ከባድ ግዴታ እንወጣለን።
ውይይት ሁል ጊዜ ተመራጭ አካሄድ ነው ያሉት አቶ ደመቀ፤ ከዚህ ኳያኢትዮጵያ ለሰላማዊ ጉዞዎች በሯ ክፍት ነው፤ከዚህ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ሁሉን ያካተተ ብሄራዊ ውይይት ለመጀመር ከአፍሪካ ህብረት እና ከአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ጋር ወደ እንሰራለን ብለዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በንግግራቸው አክለውም ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያላትን የድንበር አለመግባባት በዲፕሎማሲ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኗንም ገልፀዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሙሉ በሙሉ በራስ አቅም እየተገነባ ያለ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ፕሮጀክት ነው ያሉ ሲሆን፤ ለሁለተኛ ዓመት ሙሌትም በስኬት ማሄድ ማቸሉን አስታውሰዋል።
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤቶችን መብራ እንዲያገኙ እንዲሁም ለወጣቶቻችን ተስፋን ለመፍጠር ኢትዮጵያ በቀናነት እያደረገች ያለው ስራ በዓለም አቀፍ አካላት ፊት በፖለቲካዊ መልክ ይዞ እንዲታይ ሆኗል ብለዋል።
ከራሳችን ውሃ ስለጠጣን ነው እየተከሰሰስን ያለወነው ያለት አቶ ደመቀ፤ በአባይ እና የህዳሴ ግድበ ጉዳይ አባይን እና የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የእኛ መተማመኛ እውነት፣ ፍትህ እና ጥበብን መሰረት ያደረገው የመተባበር መንገዳችን ነው ሲሉም ተናግረዋል
በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሀገራት ጋር የጀመርነውን ድርድር መርህን ተከትለን ውይይት የምናደረግ ሲሆን ሁሉንም ተጠቃሚ እንዲያደርግ ጽኑ አቋም አለን ሲሉም ተናግረዋል።
የድርድር አጋሮቻችን ይህን በውል ተገንዝበው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት በሚካሄደው የድርድር ሂደት ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት ላይ ለመድረስ እንደሚዘጋጁ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል::
ከሰላም አስከባሪዎች ጋር በተያያዘም ኢትዮጵያ ሰራዊት በዳርፉር እነ በአብዬ ግዛት የተሰጣቸውን ሳልን የማስፈን ተልእኮ በስኬት ማጠናቀቅ ችለዋል፤ ለዚህም ከፍተኛ መሰዋእትነት ከፍለዋ ብለዋል።
ለዚህም ለኢትዮጵያ ሰራዊት ክብር አለን ያሉ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ሁሌም በእነሱ እንደምትኮራ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ጊዜ በአብዬ የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ሀይላችን የሽግግር ሂደት እየተቃረበ ከመሆኑ አንጻር፣ ሁለቱ ጎረቤቶቻችን የግዛት ባለቤትነት ጥያቄያቸው የሚፈታበትን የጋራ ተቀባይነት ያለው ሂደት እና ውጤት ላይ እንዲደርሱ መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን ብለዋል።