ፖለቲካ
በሱዳን የቀጠለው ሰልፍ የፀጥታ ኃይሎች ወደ ቤተ መንግስት የሚያስካኬዱ መንገዶችንና ድልድዮችን እንዲዘጉ አድርጓል
በጀነራል አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ምርጫ ሳይደረግ ስልጣን እንደማይሰጥ ተናግሯል
ጦር ስልጣን ወደ ሲቪል አስተዳድር እንዲመልስ ሰላማዊ ሰልፎች አንደቀጠሉ ናቸው
የሱዳን ጦር ስልጣን ለሲቪል አስተዳድር እንዲመልስ ሰላማዊ ሰልፎች አንደቀጠሉ ናቸው።
ከሶስት ወራት በፊት በሱዳን ጦር በተፈጸመ መፈንቅለ መንግስት ምክንያት በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ይመራ የነበረው የሲቪል አስተዳድር መንግስት ከፈረሰ በኋላ ሱዳን በወታደሮች በመመራት ላይ ናት።
ድርጊቱ ያስቆጣቸው ሱዳናዊያንም በየዕለቱ ስልጣን የተቆጣጠረው የሱዳን ጦር ስልጣን እንዲያስረክብ በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ናቸው።
በዛሬው ዕለትም ወታደራዊ አመራሩን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ሲሆን ጦሩ ወደ ካርቱም ቤተ መንግስት የሚያስካኬዱ መንገዶችን እና ድልድዮችን በመዝጋት ላይ ይገኛል።
የሱዳን ጦር ከዚህ በፊት በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃ 79 ዜጎች መገደላቸውን የሱዳን ሀኪሞች ማህበር ገልጿል።
በጀነራል አልቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር በበኩሉ በምርጫ ላልተመረጠ መንግስት ስልጣን እንደማይሰጥ ገልጿል።
በካርቱም ያለው የመንግስታቱ ድርጅት ቢሮ በሱዳን በሲቪሎች የሚመራ መንግስት ወደ ስልጣን እንዲመጣ ወታደራዊ አመራሮችን እና ፖለቲከኞችን በማነጋገር ላይ መሆኑን አስታውቋል።