የሱዳን ሉአላዊ ም/ቤት ሊቀ መንበር ሌ/ጄ አል-ቡርሃን ለአዳዲስ ሚኒስትሮች ሹመት ሰጡ
በሱደን እስካሁን ድረስ ስልጣን የያዘውን ወታደራዊ መንግስት የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው
ሌ/ጄንራል አል-ቡርሃን ለ15 አዳዲስ ሚኒስትሮች ሹመት መስጠታቸው ታውቋል
የሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ ሌተናል ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን አዲስ ካቢኔ ማቋቋማቸው ተነግሯል።
ሌተናል ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን የቀድሞውን ካቢኔ ከበተኑ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባቋቋሙት ካቢኔያቸው ለ15 ሚኒስትሮች ሹመት መስጠታቸውም ታውቋል።
በዚህም መሰረት አምባሳደር አሊ አል ሳዲቅ አሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው ሲሾሙ፤ ኢንጂነር ዳውል ባያት ብዱልራህማን መንሱር የመስኖ እና የውሃ ሀብት ሚኒስትር ተደርገው ተሾመዋል።
እንዲሁም ኦትማን ሁሴን ኦትማ የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ሞሃመድ ብደላህ መሃመድ የነዳጅ እና ኢነርጂ ሚኒስትር እንዲሁም ሱአድ አለ ጣይብ ሃሰን በሰራተኛ እና የአስተዳደር ሪፎም ሚኒስትርት ተሸመዋል።
ሉአላዊ ምክር ቤት መሪ ሌተና ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን በአጠቃላይ ለ15 ሚኒስትሮች ሹመት መስጠታቸውም ታውቋል።
በሌተናል ጄነራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሀን የሱዳን በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ ሀምዶክ የሚመራውን ሲቪል አስተዳደር በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከስወገደ በኋላ ካቢኔ ሲቋቋም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ጦሩ በጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ የሚመራውን የሲቪል መንግሥት በመፈንቅለ መንግሥት ካስወገደ በኋላ በሱዳን ቁጣ ተቀስቅሶ ቆይቷል።
ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ቢያንስ 70 ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸው ተዘግቧል።
በሱደን እስካሁን ድረስ ስልጣን የያዘውን ወታደራዊ መንግስት የሚቃወሙ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።