ፖለቲካ
ተመድ በሱዳን ቀውስ ጉዳይ“አስተባባሪ እንጂ አስታራቂ መሆን የለበትም"-ሱዳን
በሱዳን ጦር የሚመራው ምክር ቤት በተመድ ሽምግልና ላይ ጠንካራ መስመር አስምሯል
የሱዳን ወታደራዊ ም/ቤት በሀገር ውስጥ ጉዳይ አለምአቀፍ ጣልቃገብነትን እንደማይቀበል ገልጿል
የሱዳን ወታደራዊ ቡድን የሚመራው ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ቅዳሜ እንደተናገሩት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ልዑክ እንደ “አመቻቺ እንዲ አደራዳሪ መሆን የለበትም”በማለት ቀውሱን ለመፍታት በሚደረገው አለምአቀፍ ጥረት ላይ ጠንካራ መስመር ማስመሩን ገልጿል፡፡
በልዩ ልዑክ ቮልከር ፔርቴስ የሚመራ የተመድ ተልዕኮ ባለፈው አመት የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት በዚህ ወር ንግግር ጀምሯል።
ቀደም ሲል የሉዓላዊው ምክር ቤቱ የተመድን ተነሳሽነት በደስታ ተቀብሏል፤ ወታደራዊ ም/ቤቱ በፔርቴስ መገኘት ላይ ምንም ተቃውሞ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡
"የተባበሩት መንግስታት የተቀናጀ የሽግግር ተልእኮ በሱዳን (UNITAMS) አስተባባሪ እንጂ አስታራቂ መሆን የለበትም" ብለዋል የምክር ቤቱ ምክትል ኃላፊ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ በሰጡት መግለጫ።
ምክር ቤቱ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እየሸሸ አይደለም፤ነገርግን በሀገር ውስጥ ጉዳይ አለምአቀፍ ጣልቃገብነትን አንቀበልም ብለዋል፡፡
የዳጋሎ መግለጫ አስተያየታቸውን ለመግለጽ ያነሳሳውቸውን ነገር አላብራርም፡፡ፐርቴስ እና ምክር ቤቱ አስተያየት ለመስጠት ወዲያውኑ ማግኘት አልተቻለም።
የሉዓላዊው ምክር ቤት የተቃዋሚዎችን ሞት የሚያጣራው ኮሚቴ ቅዳሜ እለት በጃንዋሪ 17 በተደረገው የፀረ መፈንቅለ መንግስት ተቃውሞ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን የምስክሮችን ቃል መሰብሰቡን ተናግሯል።