ስፖርት
ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆነች
ደራርቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት ፌደሬሽኑን በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝደንትነት አገልግላለች
ደራርቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት ፌደሬሽኑን በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝደንትነት አገልግላለች
ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ስትመራ የቆየችው ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በይፋ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ሆና ተመረጠች።
ለቦታው ብቸኛ ተወዳዳሪ የነበረችው ደራርቱ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ 27 ድምፅ በማግኘት ነው ፕሬዝደንት የሆነችው።
ኮማንደር ደራርቱ ላለፉት ሁለት ዓመታት ፌደሬሽኑን በምክትል ተቀዳሚ ፕሬዝደንትነት አገልግላለች። ኮማንደሯ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን በዋና ፕሬዝዳንትነት ትመራለች፡፡
ደራርቱ በአውሮፓውያኑ 1992 በባርሴሎና በ10000 ሜ እንዲሁም በ2000 በሲድኒ ኦሎምፒክ ላይለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች። በኤድመንተን አለም ሻምፒዮናም የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ደራርቱ ቱሉ በተለያዩ ውድድሮችም በግሏማሸነፏ ይታወሳል፡፡