የበረሃ አንበጣ 160 ወረዳዎችን አዳርሷል-ግብርና ሚኒስቴር
የበረሃ አንበጣ 160 ወረዳዎችን አዳርሷል-ግብርና ሚኒስቴር
የበረሀ አንበጣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፤ በደቡብና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ 160 ወረዳዎችን ማዳረሱን የግብርና ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ካባ ይህን ያሉት የአለም የምግብ ድርጅት የኪራይ ዋጋዋን በመክፈል በኢትዮጵያ አንበጣ ለመከላከል ሥራ ላይ የምትሰማራ አንድ መለስተኛ አውሮፕላን ለመንግስት ባስረከበበት ወቅት ነው፡፡
ከዚህ በፊት በቅ ብሎ የሚጠፋው የበረሀ አንበጣ አሁን ላይ ከምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል አልፎ ወደ አልተለመደበት ቦታ ወደ መካከለኛውና ምእራብ ኢትዮጵያ በመስፋፋት ላይ መሆኑን ደ/ር ካባ ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ካባ የወቅቱ አየር ሁኔታና ንፋስ ወደ ምእራብ ኢትዮጵያ ለመዛመቱ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
በህብረተሰቡ አርዳታ አንበጣ የሚፈለፍልበትን ቦታ የመለየት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ዶ/ር ካባ የአለም የምግብ ድርጅት እርዳታ አንበጣ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመካለከል ብሎም ለማጥፋት ይደረዳል ብለዋል፡፡
እስካሁን 5 አውሮፕላኖች አንበጣ በመከላከል ስራ ላይ እንደተሰማሩ ገልጸዋል፡፡
የአለም የምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ፋቱማ ዲ.ሰይድ በበኩላቸው ተጨማሪ ሁለት አውሮፕላኖችን ኪራይ በመክፈል ለመንግስት እንደሚያስረክቡ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ድርጂቱ የስልጠና ድጋፍ እንደሚያርግ ገልጸዋል፡፡