ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ ቁልፍ ምዕራፎች እንዲጠናቀቁ አበረታተዋል
የህዳሴው ግድብ የስራ ክንውን ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሥራ ክንውን ሁኔታ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀረበ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የክንውን ሁኔታውን በመመልከት ሕልምን እውን ለማድረግ ውጤታማ ሥራ የማከናወንን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል።
ከአያያዝ ጉድለት የተነሣ የተከሠተውን የሥራ መጓተት አስታውሰውም፣ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የሕዳሴው ግድብ የግንባታ ሥራ የገጠመውን ችግር ለመፍታት መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃዎች ዘርዝረዋል።
ሁሉም ተቋራጮች ሥራውን ለማፋጠን በኅብረት እንዲሠሩና በቶሎ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችሉ ቁልፍ ምዕራፎችን እንዲያጠናቅቁ አበረታተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ ለኢትዮጵያውያንም ሆነ አፍሪካውያን የኩራት ምንጭ በሆነው ግድብ ፣ የተፋሰሱን ሀገራት በማይጎዳ ሁኔታ በፍትሐዊነት ለመጠቀም ያላቸውን ቁርጠኝነት አውስተዋል።